ጠቃሚ መረጃ የታፈኑ (banned) የተደረጉ - TopicsExpress



          

ጠቃሚ መረጃ የታፈኑ (banned) የተደረጉ ድረ-ገጾችን እንደት መመልከት ይቻላል? በአለም ላይ ካሉ ሀገሮች ሁሉ እጅግ በተራቀቀ መንገድ የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን በማፈንና ድረ-ገጾችን በማገድ ቻይናን የሚስተካከላት ሀገር እስካሁን ድረስ አልተገኘም። ከሁልም የሚገርመዉ ደግሞ የሀገሪቱ መንግስት ድረ-ገጾችንና ሌሎች ተዛማጅ የመረጃ ምንጮችን በማፈን (በመከልከል) ብቻ አያቆምም ከዚህ ይልቅ ታች ድረስ በመዉረድ እያንዳንዱ የሀገሪቱ ዜጋ ምን ምን አይነት ድረ-ገጾችንና የመረጃምንጮችን በቀን ዉስጥ እንደጎበኘ የተጠናከረ ቁጥጥርና ክትትል ያደርጋል። በዚሁ ያልተገባ አካሄድ የተነሳም ከሀገር ዉጭ ከሚኖሩ ቡድኖች ጋር ያልተገባ ግኑኝነትአድርጋችሗል፣ አየር ላይ (online) በተሰበሰበ አስተያየት (petition) ተሳትፋችሗል ፣ ተሀድሶ ይደረግ፣ ሙስና ይቁም በማለት ቅስቀሳ አካሂዳችሗል በሚሉና እና በሌሎች ተመሳሳይ ምክንያቶች ለእስርና እንግልት የሚዳረጉ የጋዜጠኞችና ግለሰቦች ቁጥር የትየሌሌ እንደሆነ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በቅርቡ ያወጣዉ መግለጫ ያመለክታል። ኢራን፣ ሳዉዲ አረቢያ፣ ቱርክ፣ እና ብራዚል ደግሞ ከቻይና በመቀጠል በተለያዬ መጠንና ስፋት ተመሳሳይ የኢንተርኔት አጠቃቀም እገዳን በሀገራቸዉ ዜጎች ላይ በመጣል በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ሌሎች ሀገሮች ተርታ ይመደባሉ። ዳግማዊ ቻይና የሆነችዉ ሀገራችን ኢትዮጵያም በኢንሳ (INSA) ወሮበሎች በኩል በመታገዝ መረጃን በማፈንና ድረ-ገጾችን በማገዱ ረገድ እያሳየችዉ ያለዉ እመርታ ይበል የሚያሰኝ ሲሆን አንድሰዉ ለአንድ ድረ-ገጽ የተመደበ በሚመስል መልኩ ነባርና አዳድድስ የሚከፈቱ ድረ-ገጾችንና የጡመራ መድረኮችን ሪከርድ ሊባል በሚችል ፍጥነት ከስር ከስር እየተከታተሉ በመዝጋት ወደር አልተገኘላቸዉም። መቸም በዚህ ፍጥነትና ትጋት የሚቀጥሉ ከሆነ እንኳንስ የተከፈቱትንና አየር ላይ የዋሉትን ይቅርና ገና ለመከፈት በሰዉ ልብ ዉስጥ ያሉትን ድረ-ገፆችን ጭምር ቀድመዉ በመዝጋት የአፈና ስልት መምህራቸዉ የሆነችዉን ቻይናን ሳይቀር በመቅደምና ከአለም አንደኛ በመሆን በቅርቡ እንደሚያስደምሙን ጥርጥር የለዉም። ያም አለ ይህ ግን“ከአንጀት ካዘኑ እምባ አይገድም!”እንደሉ የዚህ አይነት የመረጃ ክልከላዎችንና እገዳዎች በተጣለባቸዉ ሀገሮች የሚኖሩ በርካታ ዜጎች የተለያዩ ዘዴዎችንና የቴክኖሎጅ አማራጮችን በመጠቀምያለባቸዉን የመረጃ ረሀብ ሳያስታግሱ ዉለዉአያድሩም። በዚህም አሁን ባለንበት ዘመን መረጃን የሚፈልግን ሰዉ የሚፈልገዉን መረጃ በማፈን አልያም እንዳይታይ በመከልከል ግለሰቡ እንዳይመረጅ ማድረግ ፈጽሞ እንደማይቻል በተደጋጋሚ በተግባር አሳይተዉናል። እኛም ሰሞኑን የዚሁ የመታገድ ሰለባ የሆነችዉን“አንድ ሕዝብ አንድ ሀገር”የጡመራ ድረ-ገጽንና ሌሎች ተመሳሳይ እጣ ፈንታ የገጠማቸዉን ድረ-ገጾች የተጣለባቸዉን እገዳ በማለፍ እንደት መከታተልና መረጃን ማግኘት እንደሚቻል አንዳንድ ነጥቦችን ለማለት ወደድን። ድረ-ገጾችን እንደት መመልከት ይቻላል ብሎ መጠየቅ አንድ ሀገር ከሚኖራት ዋነኛ የድረ-ገጽ መረጃ ማስገቢያና ማስዎጫ በር (ጉሙሩከ ጣቢያ እንደማለት) ሌላ የምንፈልገዉን መረጃ ወደ ሀገር ዉስጥ አስገብተን ለማየት አልያም ወደ ዉጭ ለመላክበዋናነት ካለዉ የመግቢያና መዉጫ በር በተጨማሪ ሌላ ድብቅ በር/መሹለኪያ እንደትማግኘት (መፍጠር) ይቻላል ብሎ መጠየቅ ማለት ነዉ። ለዚህም ብዙ አማራጮችን መጠቀምና ማንሳት የሚቻል ቢሆንም የተለመዱና ቀላል ናቸዉ ያልናቸዉን ሁለት አማራጮችን ከዚህ እንዲከተለዉ እንመልከት፡ የመጀመሪያዉናምናልባትም ቀላሉ ሊባል የሚችለዉ ማየት የፈለግነዉን ድረ-ገጽ በቀትታ በራሱ የURL አድራሻ በኩል ለማየት( acess ለማድረግ) ከመሞክር ይልቅ በሌሎች ሁለተኛ ወገን በሆኑና ለዚሁ አገልግሎት ሲባል የተፈጠሩ ድረ-ገጾችን ሽፋን በማድረግ (using website proxies) ለመመልከት መሞክር ሲሆን ይህም ማለት የሌላ እንዲገባ የተፈቀደለትንና እንዳይገቡ ከተደረጉ ድረ-ገጾች መካከል ዝርዝሩ ያልተካተተን ድረ-ገጽ አድራሻ እንደሽፋን (የሌላ ሰዉን ID አሳይቶ እንደመግባት ማለት ነዉ) በመጠቀም የተከለለን ድረ-ገጽ እንዲገባ ማስቻል ማለት ነዉ። ኢንተርኔት ላይ የዚህ አይነት አግልገሎት የሚሰጡ ብዙ ድረ-ገጾች ያሉ ሲሆን ነገሩን በቀላሉ ለመረዳት እንድንችል ከዚህ የሚከተለዉን ምሳሌ እንመልከት። ለምሳሌ የተከለከለዉና ማየት የፈለግነዉ ድረ-ገጽ የማህበራዊ መረብ የሆነዉን facebook ነዉ እንበል እናም facebookየሚለዉን/ አድራሻ በቀጥታ የብራዉዘሩ አድሬሰ ባር (browser address bar) ላይ ታይፕ በማድረግ ለመክፈት ከሞከር ይልቅ ይልቅ በቅድሚያ spysurfing/(ለምሳሌ ያክል የተጠቀምነዉና ከላይ የገለጽነዉን አይነት የሽፋን አገልግሎት ከሚሰጡ በረካታ ድረገጾች መካከል አንዱ ነዉ)ድረ-ገጽን በመክፈትና በፊት ለፊት ገጹ ላይ ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀዉሳጥን ዉስጥ facebookየሚለዉን/ አድራሻ በማስገባትና በመፈለግ መክፈት ማለት ነዉ። ነገር ግን የዚህ አይነት ዘዴን መጠቀም የሚቻለዉ እንደ ተለዋጭ ፕሮክሲ በመሆን የሚያገለግለን ድረ-ገጽ (ከላይ ለቀረበዉ ምሳሌ spysurfingማለትነዉ/) በአፋኞቹ በኩል የማይታወቅና እንዲታገዱ ከተደረጉ ድረ-ገጾች ዝርዝር ዉስጥ ያልተካተተ መሆን ይኖረበታል። ይህ ካልሆነ ግን አፋኞቹ ቀድመዉ ይህንኑ ድረ-ገጽ እንዳይከፈት ስለሚከለክሉት በሱ በኩል አልፈን (ሽፋን አድርገን) የምፈልገዉን ድረ-ገጽ መመልከት አንችልም ማለት ነዉ። በመሆኑም የዚህን አይነት አገልግሎት ማግኘት የሚቻለዉ በአፋኞች አይን ዉስጥ ያልገቡ ዌብ-ፕሮክሲዎችን በመጠቀምና ተከታትለዉ ሲደርሱባቸዉና ሲያግዷቸዉ ደግሞ ሌላ አድስ ዌብ-ፕሮክሲች በመፈለግና በመጠቀም ይሆናል ማለት ነዉ። ለዚህም ሲባል በቁጥር እጅግ ብዙ የሆኑና በየቀኑ የሚፈጠሩ አዳድስ ዌብ-ፕሮክሲዎች ስላሉ የሚያፍኑ አካላት ሁሉንም ማወቅና መዝጋት ስለማይችሉ አንዱ ሲዘጋ ሌላ እየቀያየርን መጠቀም እንችላለን ማለት ነዉ። ሌላዉና ምናልባት ከላይ ከቀረበዉ አማራጭ የተሻለ እንደሆነ የሚታመነዉ ደግሞ ዌብ ሳይቶች እንደሽፋን ከመጠቀም ይልቅ ለዚሁ አገልግሎት ተብለዉ የተሰሩ ሶፍትዌሮችን ማዉረድና መጠቀም ነዉ። ለዚህም ከላይበቁጥር አንድ የተመለከትናቸዉን የድረ-ገጽፕሮክሲዎችን ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ እንደ ዋነኛ ድክመት ከሚጠቀሱ በረካታ ነገሮች መካከል አንዱና ዋነኛዉ እነዚህ ድረ-ገፆች የሽፋን አገልግሎቱን ከመስጠት ጎን ለጎን የተለያዩ ማስታወቂያዎችን ድረ-ገጾቹን ለሚጠቀሙ ሰዎች ስለሚያስተላልፉ አላስፈላጊ የኔትወርክ መጨናነቅን የሚፈጥሩ መሆናቸዉ ነወ። ይህንን አላስፈላጊ የማስታዎቂያ ሽፋን ለማስዎገድ ደግሞ ለዚሁ አገልገሎት ተብለዉየተዘጋጁ ሶፍትዌሮችን በማዉረድና ኮምፒዉተራችን ላይ በመጫን እንዳማራጭ መጠቀም እንችላለን። ነገር ግን እነዚህ አይነት ሶፍትዌሮች ተጨማሪ ማስተካከያዎችን(configuration) ስለሚጠይቁ እንደላይኛዉ አማራጭ ቀላል ላይሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ የዚህ አይነት አገልግሎት ከሚሰጡ ሶፍትዌሮች መካከል ultra surf የሚባለዉ ሶፈትዌር በብዛት አገልገሎት ላይ የዋለና የተሻለ የሚባል ሲሆን ይህን ሶፍትዌር በመጠቀም የተከለከሉ ድረ-ገጾችንለመጎብኘት ኮምፒዉተራችንን ከዚህ እንደሚከተለዉ በማስተካከል መጠቀም እንችላለን A. በቅድሚያ የቅርብ ጊዜ ቨርዠን የሆነዉን ultra surf ሶፍትዌር ማዉረድ (የሶፍትዌሩ ሳይዝ (መጠን) በኪሎ ባይት ደረጃ ሲሆን ዚፕድ (zipped) የሆነዉን ፋይል በቀላሉ ጉግል ላይ ultra surf የሚል ዋና ቃል ታይፕ በማድረግና በመፈለግማዉረድ ይቻላል) B. በመቀጠል ያወረድነዉን zipped ፋይል unzip በማድረግ የሶፍትዌሩ ተፈጻሚ የሆነዉን ፋይል (excutable file) በኮምፒዉተራችን ላይ ስናሮጠዉ ( run ስናደረገዉ) connecting to the server የሚል መልዕክት (messege) የያዘ ዲያሎግ ቦክስ ይመጣልናል። C. በማስቀጠል sussusfully connected to the server የሚል መልዕክት እዚሁ ድያሎግ ቦክስ ላይ እስከምናይ ድረስ በትግስት መጠበቅ ይኖረብናል። D. sussusfully connected to the server የሚለዉን መልዕክት ካገኘንበሗላ በቀጥታ ዌብ ብራዉዘራችን በመክፈትና ተገቢዩን የፕሮክሲ አድራሻና የፖረት ቁጥር በመስጠት ማስተካከል (configure) ማድረግ ይኖረብናል። ለምሳሌ የምንጠቀመዉ ዌብ ብራዉዘር Mozila firefox ቢሆን እንደሚከተለዉ ማስተካከል እንችላለን። (ዌብብራዉዘራችን internet explorerከሆነ ግን ultra surf እራሱ አዉቶማቲካሊ configure ስለሚያደርግልንይህን አካሄድ ተግባራዊ ማድረግ ላይጠበቅብን ይችላል።) posted by: Asif Asim
Posted on: Wed, 06 Nov 2013 06:17:17 +0000

Recently Viewed Topics




© 2015