ፍቅር ማለት ሌሎች እኛን መውደዳቸው - TopicsExpress



          

ፍቅር ማለት ሌሎች እኛን መውደዳቸው ሳይሆን እኛ ሌሎችን መውደዳችን ነው፡፡ ፍቅር መልካሙን ሁሉ የሚያጣፍጥ ቅመም ነው፡፡ ይህች ዓለም ስታልፍ ኢትዮጵያም ታልፋለች፡፡ ለዘላለም የሚኖረው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ፍቅር የጦር መሣሪያ የላትም፣ የጦር መሣሪያ የያዘውን ግን ትማርካለች፡፡ ፍቅር ከሐኪሙ ኪኒን ይልቅ በሽተኛን ትፈወሳለች፡፡ ከዳኛው ቃል ይልቅ እስረኛን ትፈታለች፡፡ ከወጌሻው ይልቅ የተሰበረውን ትጠግናለች፡፡ ፍቅር ቀጣይ የሚሆነው በይቅርታ ነው፡፡ መንገድ የሚረዝመው በድልድይ ነው፡፡ ፍቅርም የሚረዝመው በይቅርታ ነው፡፡ የፍቅር ፍጻሜው ንብረት መስጠት አይደለም፡፡ ፍቅር ራሱን ይሰጣል፡፡ ራሱንም ይቀበላል::
Posted on: Thu, 24 Oct 2013 08:46:28 +0000

Recently Viewed Topics




© 2015