BY ADDIS MAMO Rate This * ባድመን መልሶ - TopicsExpress



          

BY ADDIS MAMO Rate This * ባድመን መልሶ ለማስረከብ ድርድር…. ተስፋዬ ኒውስ በሚል የሚታወቅ ድረገጽ ኢትዮጵያ ኤርትራን ለማግባባትና ወደ ድርድር ለማምጣት 250 ሜጋ ዋት የኤሌልክትሪክ ሃይል በነጻ እንደምትሰጥ የኤርትራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኡስማን ሳለህን ጠቅሶ ዘግቧል። ለንዶን በተካሔደ የኤርትራ ተወላጆች ዓመታዊ ፌስቲቫል ላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ የተባለው እውነት ከሆነ ኢህአዴግ ባድመን ጨምሮ ኤርትራ የኔ የምትላቸውን ቦታዎች ለማስረከብ መስማማት አለበት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትንም ከስፍራው ላመንሳት ይስማማል። ኤርትራን ወደ ሰላም ንግግር ላማምጣት ተደረገ በሚባለው በዚህ የማግባቢያ ስምምነት ላይ ድረ ገጹ ከኢትዮጵያ ወገን ማረጋገጫ አልጠቆመም። ወይም አሸናጋይና ሃሳቡን ያቀረቡ ናቸው ከተባሉት ሩሲያ፣ ቱርክና ኳታር ወገኖች የተሰጠ ነጻ አስተያየት አላካተተም። ኢህአዴግም ዜናውን አስመልክቶ በይፋ ያስተባበለው ነገር ስለመኖሩ የተሰማ ነገር የለም።ይሁን እንጂ የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በሎንደን ከወገኖቻቸው ጋር መሰብሰባቸውና በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መናገራቸው እውነት ነው። በኤርትራ የኑሮ ውድነትና ችግር በቃላት ሊገለጽ ከሚችለው በላይ አስቸጋሪ ደረጃ ላይ በመድረሱ ሻዕቢያ ካትዮጵያ ጋር ያለውን ችግር ለመቋጨት ከመቼውም ጊዜ በላይ ፍላጎት እንዳለው የሚገልጹ ክፍሎችም አሉ።
Posted on: Sun, 28 Jul 2013 18:41:27 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015