Eritrea: Hail storm dumps metre of ice on capital | - TopicsExpress



          

Eritrea: Hail storm dumps metre of ice on capital | በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ባልተለመደ ሁኔታ በጣለው ከባድ ዝናብ ከተማዋ በበረዶ ግግር መሸፈኗ ተገለጸ፡፡ በከተማዋ የጣለው በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ እስከ አንድ ሜትር የሚደርስ የበረዶ ግግር ማስከተሉ ነው የተገለጸው፡፡ ቢቢሲ እንዳለው ከሆነ በአስመራ ይህን መሰሉ ሃይለኛ ዝናብ ሲያጋጥም ለመጀመሪያ ግዜ ሲሆን በያዝነው ወቅት በአስመራ ከተማ ከባድ ዝናብ መዝነቡ ወቅቱን ያልጠበቀ እንደሆነ እና በከተማዋ መንገዶች ላይ የሚታየው የበረዶ ግግርም እግረኞችን አላላውስ ከማለቱ በተጨማሪ ለመኪኖችም ስጋት ሆኗል ነው የተባለው፡፡ በኤርትራ ከየካቲት እስከ ሚያያዝያ ያለው ወቅት ዝቅተኛ የዝናብ ሁኔታ የሚታይበት ወቅት ሲሆን ይህን የመሰለ ከባድ ዝናብ መጣሉ ግን የከተማዋን ነዋሪዎች አስደንቋል፡፡ የቢቢሲ ዘገባ ዝናቡም ይሁን በረዶው በሰው ህይወትም ይሁን በንብረት ላይ አደጋ ማድረሱን እና አለማድረሱን አልገለጸም፡፡ ለተጨማሪ…. diretu.be/678567
Posted on: Sat, 15 Mar 2014 19:10:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015