Foreign Ministers Of Ethiopia, Kenya, Uganda And US Agree To Stop - TopicsExpress



          

Foreign Ministers Of Ethiopia, Kenya, Uganda And US Agree To Stop Killings In South Sudan ... See at... diretu.be/558743 |ኢትዮጵያ፣አሜሪካ፣ኡጋንዳና ኬንያ በደቡብ ሱዳን በአፋጣኝ የሰላም አስከባሪ ሃይል እንዲሰማራ ተስማሙ የኢትዮጵያ፣የአሜሪካ፣የኡጋንዳና የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በደቡብ ሱዳን ያለው ግጭት እንዲያበቃና በአገሪቱም የሰላም አስከባሪ ሃይል በአፋጣኝ እንዲሰማራ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በደቡብ ሱዳን ባለው ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአሜሪካው አቻቸው ጆን ኬሪ፣ከኬንያዋ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚና መሃመድና ከኡጋንዳው ሳም ኩቴሳ ጋር አዲስ አበባ ውስጥ በዝግ መክረዋል። ከምክክሩ በኋላ አጭር መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ሚኒስትሮቹ በደቡብ ሱዳን እየተባባሰ የመጣው ግጭት በአገሪቱ ሰብዓዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ከማስከተል ባሻገር ለአካባቢው አገራት የስጋት ምንጭ እየሆነ በመምጣቱ ግጭቱ ዘላቂ እልባት የሚያጋኝበትን ዘዴ በጋራ በማፈላለግ ዙሪያ በቅርበት ተባብሮ ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰዋል። በደቡብ ሱዳን የተፈጠረውን ቀውስ ለማስቆም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካኝነት አፋጣኝ የሰላም አስከባሪ ሃይል እንዲሰማራም ስምምነት ተደርሷል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በበኩላቸው በደቡብ ሱዳን በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እንዲያበቃ፣በግጭቱ ተጎጂ የሆኑ አካላት ሰብዓዊና ቁሳዊ ድጋፍ እንደሚያገኙ የእርዳታ ድርጅቶች የመተላለፊያ መስመሮች እንዲያገኙ ተቀናቃኝ ወገኖች መተባበር እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል። ከነገ በስቲያ ወደ ጁባ በመጓዝ ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ጋር በአገሪቱ ያለው ግጭት በአፋጣኝ በሚቆምበት ጉዳይ ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።
Posted on: Fri, 02 May 2014 12:00:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015