The 2nd Phase of Addis Ababa Mobile Network Expansion is Completed - TopicsExpress



          

The 2nd Phase of Addis Ababa Mobile Network Expansion is Completed ... See at ... diretu.be/339358 | ኢቲዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ሲያካሄደው የነበረው የሁለተኛው ምዕራፍ የማስፋፊያ ፕሮጀክት መጠናቀቁ ተገለጸ *ኢትዮ ቴሌኮም በህንጻዎች ላይ አንቴና ለመትከል እክል ገጥሞኛል ብሏል አቲዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ሲያካሄደው የነበረው የሁለተኛው ምዕራፍ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጠናቅኩኝ ብሏል። የኢቲዮ ቴሌኮም የህዝብ ግንኙነት ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፤ ፕሮጀክቱ 239 የአዲስ አበባ አካባቢዎችን ሰፊ የኔትወርክ አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል ብለዋል። አቶ አብዱራሂም አክለውም ቀደም ሲል በተከናወነው የመጀመሪያ ዙር የማስፋፊያ ስራ 75 የከተማዋ አካባቢዎች ቀልጣፋ የኔትወርክ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል። በቀጣይ በሶስተኛው ምዕራፍም ከዚህ በፊት የኔትወርክ አገልግሎት ያላገኙ አዳዲስ አካባቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እንዲሁም የ4ጂ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስራ እየተከናወነ መሆኑንም የዘገበው ኤፍቢሲ ነው። በሌላ በኩል ኢቲዮ ቴሌኮም በሶስተኛው ዙር የማስፋፊያ ፕሮግራም በትላላቅ ህንጻዎች ላይ የኔት ወርክ አንቴና ለመትከል ለባለህንጻዎቹ ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ነኝ ቢልም እክል እየገጠመው መሆኑን አስረድቷል …. ስለ አንቴና ተከላው እና የኢቲዮ ቴሌኮም ገጠመኝ ስላለው እክል ሙሉ ዘገባውን ይከታተሉ፡፡
Posted on: Fri, 02 May 2014 20:30:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015