The authority banned 12 mln birr worth of food and medicines from - TopicsExpress



          

The authority banned 12 mln birr worth of food and medicines from entering the country | Read at .... goo.gl/FK1yBV | 12 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ምግቦችና መድኃኒቶች አገር ውስጥ እንዳይገቡ ተደረገ ተባለ ምግብና መድኃኒቶቹ እንዳይገቡ የተደረገው የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈ፣ ሌብሊንግ የሌላቸው፣ ሌብሊንጋቸው ባለሥልጣኑ ባስቀመጠው መሥፈርት መሠረት በእንግሊዝኛ ወይም በአማርኛ መሆን ሲገባው ከዚህ ውጪ በመሆኑና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣንን መግለጫ ጠቅሶ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል፡፡ ከተጠቀሰው የገንዘብ ግምት ሰባት ሚሊዮን ብር የሚሆነው መድኃኒት ነውም ተብሏል፡፡ መድኃኒቶች ከቻይና ወይም ከህንድ የገቡ ሆነው ሳለ፣ የተሳሳተ ሌብሊንግ በማድረግ አውሮፓ የተሠሩ አስመስሎ እንደሚቀርብም ተገልጿል፡፡ ዕቃዎቹ የተያዙት በአምስት ኬላዎች ሲሆን ኬላዎቹ አዳማ፣ ሞጆ፣ አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት፣ ቃሊቲና ገላን ናቸው፡፡ በሌላ በኩል 81.555 ሜትሪክ ቶን የሚሆኑ የተለያዩ ምግቦች (ሩዝ፣ ስኳር፣ ጆሊጁስ፣ ቸኮሌት) አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ሌብሊንጋቸው እንግሊዝኛም አማርኛም ባለመሆኑ የተወሰነው ወደመጣበት አገር እንዲመለስ፣ ቀሪው ደግሞ በአገር ውስጥ እንዲወገድ መደረጉን ባለሥልጣኑ መግለጹን የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ጠቁሟል፡፡
Posted on: Wed, 13 Aug 2014 20:00:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015