Violence will not solve the Addis Master plan Controversy: ...See - TopicsExpress



          

Violence will not solve the Addis Master plan Controversy: ...See at .... diretu.be/539398 | የኦሮሚያ እና የአዲስ አበባ ረቂቅ ማስተር ፕላን ጉዳይ በሁከት እንደማይፈታ በኦሮሚያ ክልል የተደራጁ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ በሚሆንበት ጉዳይ ላይ ውይይት እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ የኦሮሚያ ከተሞችን ልትጠቀልል ነው በሚል በተለያዩ የኦሮሚያ ዩኒቨርስቲዎች ተቃውሞ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳ ማስተር ፕላኑን ተግባራዊ ለማድረግ ውይይት እየተካሄደ ቢሆንም ተማሪዎች የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት እንዲሁም ትምህርት በማቋረጥ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ለሰንደቅ ጋዜጣ አስተያየታቸውን የሰጡት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የመላው ኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኦህዴፓ) ጉዳዩ በሁከት ሊፈታ እንደማይችል እና መንግስት የተማሪዎቹን ጥያቄ በሰለጠነ መንገድ እንዲፈታው ጠይቀዋል፡፡ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለጹት ‹‹ የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ጉዳይ በሁከት አይፈታም›› ብለዋል፡፡ ፓርቲው ከሌሎች ሦስት የኦሮሞ ፓርቲዎች ጋር በመሆን ተወያይቶ አቋሙን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለፌደሬሽን ምክር ቤት እንዲሁም ለኦሮሚያ ክልል ደብዳቤ በመጻፍ እንዲደርሳቸው መደረጉን ገልጸዋል፡፡ እኛ የኦሮሚያ ድንበር ተከብሮ ልማቱ ቢካሄድ ተቃውሞ የለንም ብለዋል ሊቀመንበሩ፡፡ የመላው ኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኦህዴፓ) በበኩሉ የተማሪዎቹ እንቅስቃሴ በሰለጠነ መንገድ መፈታት አለበት ብሏል፡፡ …. diretu.be/539398
Posted on: Wed, 30 Apr 2014 09:00:00 +0000

Recently Viewed Topics




© 2015