Women in Ethiopia struggle to survive without water ... See at ... - TopicsExpress



          

Women in Ethiopia struggle to survive without water ... See at ... diretu.be/682436 | በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሴቶች የውሃ እጥረት ከፍተኛ ጫና እያሳደረባአው እንደሆነ አንድ ዘገባ አመልክቷል፡፡ በደቡብ ኢትዮጵያ የኮንሶ አካባቢ ንጹህ ውሀ ማግኘት የሴቶች ከባዱ ፈተና መሆኑን ያመላከተው ዘገባው ንጹህ ውሃ ማግኘት በቀላሉ የሚታሰብ አለመሆኑን የአካባቢውን ሰዎች ዋቢ በማድረግ አምልክቷል፡፡ ንጹህ ውሀ መፈለግ እና ሴቶች የተሳሰሩ መሆናቸው የተጠቆመ ሲሆን 13 ሺ ነዋሪዎች በሚኖሩባት የጃርሶ አካባቢ ችግሩ የጎላ መሆኑን ያመለክታል፡፡ በአካባቢው ከቅርብ ግዚያት ወዲህ የተስተዋለው የዝናብ እጥረት የአካባቢውን ሴቶች የስራ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረው እና በአካባቢው ለእናቶች እና ህጻናት ሞት ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚዝም ዘገባው አመልክቷል፡፡ በኢትዮጵያ ከ 40 አመታት በላይ በውሃ አቅርቦት ዙሪያ ሲሰራ የቆየው ወተር ኤይድ (WaterAid ) በአካባቢው የሚስተዋለውን የንጹህ የመጠጥ ውሃ እጥረት ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑም ተጠቁሟል በኢትዮጵያ የውሃ ሽፋን እ.ኤ.አ ከ1990 ወዲህ በአራት እጥፍ የጨረ ቢሆንም አሁንም በሃገሪቱ ንጹህ የመጠጥ ውሃ የሚያገኙ ዜጎች ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው፡፡ ለዝርዝሩ ለዝርዝሩ ......diretu.be/682436http
Posted on: Wed, 14 May 2014 10:29:28 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015