ሱብሂ በጀምዐ የማንሰግድ ሰዎች በተለይ - TopicsExpress



          

ሱብሂ በጀምዐ የማንሰግድ ሰዎች በተለይ ወንዶችን ይመለከታል ***አንድ ጊዜ አብደላህ ኢብን ኡሙ መክቱም(ረ.ዐ) መልእክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ መጡና “አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሱብሂ ሰላትን ቤቴ እንድሰግድ ይፈቅዱልኛል ?” ብለው ጠየቋቸው፡፡ አብደላህ እውር ናቸው በዛ ላይ በረሃ በሆነችው መካ ከተማ ጊንጥ፣ እባብ የመሳሰሉት ጎጂ እንስሳቶች ነበሩባት፡፡እንደ አብደላህ ለማያይና ዱላ ተሸክሞ ለሚሄድ ደካማ ሰው ይቅርና ለአይናማውና ጠንካራ ሰው ከባድ የሆነ መንገድ ነው፡፡ገር የሆኑት መልዕክተኛው ችግራቸውን ተረድተው “ቤትህ ስገድ” ካሉት በሗላ “አዛን ትሰማለህ እንዴ?” ብለው ጠየቁት፤ አብደላህም “አዎ እሰማለሁ” ሲል መለሰ፡፡መልዕክተኛውም “በል አዛን ሰምተህማ እየተንፉቀክም ቢሆን ና(ለአዛኑ ምላሽ ስጥ)” አሉት፡፡ ለዛ ለእውሩ እንዲ ከሆነ ለኛስ ? ቀኑም ማታውም ቀን በሆነበት ዘመን፣ መስጂድ በየቦታው በተስፋፋበት ዘመን፣ ጤንነት አላህ ሰቶን ባለንበት ተጋድመን ሱብሂ ሰላትን ስናሳልፈው የሚቀፍ አይመስላቹም ? ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) “ሱብሂ ሰላት ቤታቸው የሚሰግዱ ወንዶች፤ ሴቶች ህጳናቶችና አዛውንቶችን ብዬ እንጂ ቤታቸውን ላቃጥል ወደድኩኝ” ብለዋል፡፡አስቡት እንግዲ ዱንያ ላይ እቤት መቃጠል ሚያስከትል አኼራስ ? ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) “ለሙናፊቆች ኢሻና ሱብሂ ሰላት መስጂድ መቶ መስገድ ይከብዳቸዋል” ብለዋል፤ አስተውል ወንድሜ ንፍቅና ምን ያህል ከባድ ወንጀል እንደሆነ!! አይሁዶች “እኛ ሙስሊሞችን ምንፈራው ሱብሂ ሰላትን እንደ ጁምዐ ተሰባስበው ሲሰግዱ ብቻ ነው” ያሉት ይህን ሁኔታችን ተረድተው ሳይሆን አይቀርም፡፡ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) “ዱንያና ውስጧ የያዘችው ሁሉ ከሚሰጠኝ የሱብሂ ቀብልያ መስገድ ይበልጥልኛል” ብለዋል፤ ወንድሞች የሱብሂ ሱናው ይህን ያህል ከሆነ ፈርዱ ምን ሊያህል እንደሚችል አስበነዋል ? ብቻ አላህ ያውቃል!!! በሌላ ሀዲስ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) “የሱብሂንና የኢሻን ሰላት ጥቅም ሰዎች ቢያውቁ ኖሮ ቢታመሙ እንኳ እየተንፏቀቁ መስጂድ ይመጡ ነበር” ሳንታመም፣ በጤንነት መተኛታችን ለረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ንግግር ክብር ያሳጣነው ይመስላል፤ ወንድሞቼ ከአላህ ጋር ከመተሳሰባችን በፊት እዚሁ ብንተሳሰብ ይሻላል፡፡ በመጨረሻም አንድ ሼህ ፈረንሳይ ሀገር በሚገኝ መስጂድ የሱብሂ ሰላት ካሰገዱ በሗላ የመጣው ሰው አነስተኛ መሆኑን አይተው ትምህርት ሲሰጡ ያሉትን ልንገራቹ “እኛ ሙስሊሞች የሸይጣን ሽንት ቤት ከሆንን ሰነበተ” አሉ፡፡የዚን ጊዜ አንድ ወጣት ልጅ “እንዴት ይህን ሊሉ ቻሉ?” ሲል ጠየቃቸው፤ ሼሁም ቡሀሪ ላይ የተጠቀሰውን ሀዲስ አስታወሱት፤ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሱብሂ ሰላት ተኝቶ ስለሚያመልጠው ሰው ሲነገራቸው “እሱ ሸይጣን ሁለቱ ጆሮዎች ላይ የሸናበት ነው” አሉ፡፡ታዲያ አንድ ቀን ሱብሂ ሲያመልጠን ሸይጣን በሁለቱም ጆሮዋችን ላይ ሚሸና ከሆነ፤ ሁለትና ሶስት ጊዜ ሲያመልጠን “የሸይጣን ሽንትቤት” መባላችን ቀንድ ያወጣ እውነት ከመሆኑም ባሻገር የቅጣት ሰለባ ከመሆንም አንድንም፡፡ ታዲያ ማነው online አምስት ወቅቱም ሰላት በሰዐቱና በቦታው ለመስገድ “ insha allah” እያለ ለሌሎች ሚያሰማ? ሴቶችም like ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ =============== ★★ምንጭ፡-peace tv amharic ★★
Posted on: Sat, 03 Aug 2013 14:53:20 +0000

Trending Topics




© 2015