ትላት ጁምአ በፍልውሃ ቶፊቅ መስጂድ እና - TopicsExpress



          

ትላት ጁምአ በፍልውሃ ቶፊቅ መስጂድ እና በተለያዩ አካባቢዎች በመንግስት ሃይሎች የታሰሩት ሙስሊሞች ፍርድ ቤት ቀረቡ: ፡ በአዲስ አበባ ከተማ ትላት ጁምአ መደበኛ የጁምአ ሰላታቸውን ለመስገድ በፍልውሃ ቶፊቅ መስጂ የተሰባሰቡ ሙስሊሞች ላይ የመንግስት ሃይሎች መስጂዱ ውስጥ ድረስ በመግባት በርካታ ሙስሊሞችን መደብደባቸው እና ማሳራቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ በርካቶች ከፍልውሃ ቶፊቅ መስጂድ እና ከተለያዩ ቦታዎች በመንግስት ሃይሎች ታፍነው የታሰሩት ሲሆን በዛሬው ዕለት ቅዳሜም ቂርቆስ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ምንጮች አስታውቀዋል|፡፡ ፖሊስም ምርመራዬን ለማካሄድ 10 ተጨማሪ ቀናቶች ይሰጠኝ በማለት በጠየቀው መሰረት የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተሰቶት ታሳሪወቹ ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል፡፡ በማሰር በመደብደብ ሰላማዊ ትግላችንን ማስቆም አትችሉም!!! አላህ ይርዳቸው!!! ድል ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች!!! አላሁ አከበር!!! Like ☑ Comment ☑ Share ☑ for more information like this page https://facebook/abudawdosman
Posted on: Sat, 03 Aug 2013 16:35:48 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015