ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ - TopicsExpress



          

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!! የመንግስት ምላሽ አሁንም ኀይልና ድብደባ ሆኗል!! በሺዎች የሚቆጠሩት በአስቃቂ ሁኔታ፤ ተደበደቡ፤ ታሰሩ፤ ቆሰሉም!! የዛሬውን የአዲስ አበባ እስታዲየም ክስተትን “ፈስቢር” እንደሚከተለው ታቀርበዋለች፡፡ የአዲስ አበባ ሙስሊሞች፤ ገና ጠዋት 12 ሰዓት አካበቢ፤ ሱብሂ ሰላት ሰግደው እንዳበቁ ነበር ወደ እስታዲየም ማምራት የጀመሩት፡፡ ሁሉም ከያሉበት ወደ እስታዲየም መገስገሱን ተያያዙት፡፡ ነገር ግን አዲስ አበባ እስታዲየም ከመድረሳቸው፤ በኪሎ ሚትሮች ርቀት ላይ የአዲስ አበባ ፖሊሶችና የፌደራል ፖሊሶች ወደ እስታዲየም የሚያዳርሱትን ጎዳናዎች ሙሉ ለሙሉ ዘግተው ነበር የጠበቋቸው፡፡ እነዚህ ፖሊሶች በተለያዩ ርቀቶች ላይ እስታዲየም አቅራቢያ እስኪደረስ ድረስ በርካታ የፍተሻ ኬላዎችን ያቆሙ ሲሆን፤ ይህም በእስታዲየሙ በአራቱም አቅጣጫዎች ተግባራዊ ሆኗል፡፡ ለምሳሌ፤ ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና የሚመጡ ሰዎች ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አካባቢ የመጀመሪያ ፍተሻ የተካሄደባቸው ሲሆን፤ በመቀጠልም እስታዲየም እስከሚደርሱ ድረስ በርካታ ጊዜ ተፈትሸዋል፡፡ ከአንዋር መስጂድ በተክለሃይማኖት በኩል የሚመጡ ሰዎችም፤ ከጎማ ቁጠባ፤ አካባቢ ጀምሮ እስታዲየም እስከሚደርሱ ድረስ በርካታ ጊዜ ተፈትሸዋል፡፡ ህዝቡ ወደ እስታዲየም እያመራ ባለበት ወቅት ላይ ለበርካታ ጊዜ ፖሊሶች ሙስሊሞችን ለመተንኮስ ቢሞክሩም ሙስሊሙ በትዕግስት አልፏቸዋል፡፡ ወደ እስታዲየም የሚሄዱትን እንዳንድ ሰዎችንም እየመረጡ ለማሰር ሞክረው የነበረ ሲሆን፤ በሙስሊሙ ርብርብ ሊለቀቁ ችለዋል፡፡ ህዝቡ ወደ እስታዲይም አካባቢም ከደረሰ በኋላ ቀድመው የሚፈልጓቸውን ሰዎች መርጠው ካስገቡ በኋላ፤ በስተመጨረሻም፤ የተቀረው ሙስሊም በከፍተኛ ፍተሻ እንዲገባ ፈቅደዋል፡፡ ሰላቱ የተሰገደው 2፡40 አካባቢ ሲሆን፤ ከሰላቱ በፊትም የተለያዩ የህገወጡ መጅሊስ ባለስልጣናት ንግግር ለማድረግ ሞክረው ህዘቡ በተክቢራ በተደጋጋሚ ተቃውሟቸዋል፡፡ ተናጋሪዎቹ ግን ሰሚ ባይኖራቸውም ዝም ብለው መናገራቸውን ቢቀጥሉም ህዝቡ እስከመቸጨረሻው ድረስ፤ ተክቢራ በማድረግና አንዳንድ መፈክሮችን በማሰማት አስቁሟቸዋል፡፡ ሰላቱ ተሰግዶ ካበቃ በኋላም፤ ሙስሊሙ ሰላማዊ ተቃውሞውን በደማቅ ሁኔታ ማሰማት የጀመረ ሲሆን፤ በዛሬው ተቃውሞ ላይ የተለያዩ መፈክሮችን አንግቦ ነበር፡፡ “ሹመኞችን አውርደናል” “መጅሊስ አይወክለንም”፤ “የታሰሩት ይፈቱ” የሚሉና ሌሎችም በርካታ መፈክሮችን አሰምቷል፡፡ በተቃውሞው ላይ በርካታ ሙስሊሞች ለሀገራቸውና ለባንዲራቸው ያላቸውን ፍቅር ለማሳየት፤ ባንዲራዎችን በክብር ሲያውለበልቡ ተስተውለዋል፡፡ ህዝቡ መፈክሩን እያሰማ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መጓዙን ቀጠለ፡፡ ነገር ግን ወደ ብሄራዊ ቲያትር ቤት አካባቢ ሲደርስ፤ የህዝቡን ሰላማዊነት ያልወደዱት፤ ፖሊሶች ህዝብን መደብደብ ተያያዙት፡፡ እጅግ በጣም ብዛት ያላቸው ሙስሊሞች በወፍራም አጠናዎች ጭንቅላቶቻቸውና መገጣጠሚያዎቻቸው እየተመረጡ በአሰቃቂ ሁኔታ ልክ እንደ እባብ ተደበደቡ፡፡ ትእይንቱ በጣም የሚያሳዝን ነበር፡፡ ሙስሊሞች የዚህ ሀገር ዜጋ አይደሉምን? ከማለትም አልፎ የሰው ልጆችስ አይደሉምን? እስከሚባል ድረስ ጥያቄ የሚያስነሳ ድርጊት ነበር፡፡ ሽማግሌዎች፤ እናቶች፤ ሴቶችና ህፃናት ሳይቀሩ ፖሊሶች በያዙት አጠና ያለ ርህራሄ ተደብድበዋል፡፡ በርካታ ሴት እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን፤ ሌሎች ሲደበደቡ በማየታቸው ብቻ እራሳቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው፤ እሪ ብለው ሲያለቅሱና በእንባ ሲታጠቡ ተመልክተናል፡፡ ብዛት ያላቸው ሴቶች ወድቀው እጅና እግሮቻቸው ተሰብረዋል፤ ቆስለዋልም፡፡ በርከታ ህፃናት ከእናቶቻቸው እና አባቶቻቸው ጠፍተዋል፡፡ ብዙዎቹ ልብሶቻቸውን፤ ጫማዎቻቸውንና ንብረቶቻቸውን ጥለዋል፡፡ እጅግ በጣም የሚያሳዝንና የመንግስትን አረመኔያዊነትን በግልጽ ያሳየ ክስተት ነበር!! በዛሬው አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችንና ወንድሞቻችን እንዲሁም፤ ህፃናትና አባቶች ሳይቀሩ በፖሊሶች ተይዘው ታስረዋል፡፡ ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!! ================== ስለ ሙስሊሙ ወቅታዊ መረጃ፤ በበቂ ሁኔታ ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ክሊክ ያድርጉና የፈስቢርን ፔጅ like ያድርጉ => m.facebook/fesbir https://facebook/fesbir
Posted on: Thu, 08 Aug 2013 08:53:21 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015