እንዲህ እየተሰቃየን የአላህ ዝምታ - TopicsExpress



          

እንዲህ እየተሰቃየን የአላህ ዝምታ በምን ይተረጎማል???????? ግዙፍ የአላህ እርዳታ ነው፡፡ የፍጥረተ-ዓለሙን ነባርና ሙት የጃሂሊያ ቅሪት ስርዓት (system) ሙሉ በመሉ በአምላካዊው ፍንትው ያለ ብርሀን የሚለውጥ ሰማያዊ ጀብዱ ነው፡፡ ‹‹ነስር›› ይሄኔ ታዲያ ታሪክ የተባ ብዕሩን ይዞ ለቀጣይ ትውልድ ለማሳለፍ አደራን ይረከባል፡፡ በደማቁም ይመዘግበዋል፡፡ በአምባገነኖችና ደካማ አማኞች መሀል በተደረጉም እየተደረጉ ባሉ ፍልሚያዎች ‹‹ማሰቢያቸውን›› መሳሪያና የወታደራቸውን ብዛት ያደረጉ ባለ ‹‹mini-brains››መውደቂያቸው ብዙውን ጊዜ የናቁት እንቅስቃሴ ነው፡፡ ነስር ሲመጣ ግን የአማኞችን ትዕግስት ተፈታትኖ፤ጉልበታቸውን አርበትብቶና፤ነፍስያቸው ከጭንቀት ብዛት ጉሮሯቸው ከደረሰች በኋላ ነው፡፡ ምናልባትም ደግሞ ህይወታቸው አልፎ፤ደማቸው ፈሶና ደብዛቸው ጠፍቶ ከነርሱ በኋላ ያለው ትውልድ ነስርን ሊያገኝ ይችላል፡፡ ለዚህ ነው እኛ መስራትና ማለፍ ብቻ ያለብን፡፡ የነስር ግንዛቤያችን እስከዚህ ድረስ ሊለጠጥ ይገባል፡፡ ነስር ድርስ ጉርስ አይደለም፡፡ በኢስላማዊው ጎዳና የሚታገሉ ታጋዮች የሚታገሉት ህይወታቸውን ሰውተው ለትውልድና ለዩኒቨርሱ ህልውና የሆነውን ‹‹ዓቂዳን›› ለመታደግ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ላይ ወደዚያኛው ዓለም የተሸጋገሩ ሰማዕታት ሙታን ተብለው አይጠሩም፡፡ ምክንያቱም ቁርአን ህያውያን ናቸው ስላለ፡፡ በኢስላም ውስጥ ኪሳራ ተብሎ ሂሳብ የለም፡፡ ሁሉንም የሚያጋጥሙ መከራዎች ‹‹በሶብር›› ካለፏቸው ምንዳው ያለገደብ ነው፡፡ ታዲያ ይህ ግዙፍ ነስር በአማኞች ልቦና ውስጥ ገደብ የለሽ ፍሰሀን ያመጣል፡፡ ኩራትና የበላይነት ስሜት በአማኞ.
Posted on: Thu, 05 Sep 2013 15:43:43 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015