ክብር ለነቢዩ ሙሐመድ!!! إِنَّا - TopicsExpress



          

ክብር ለነቢዩ ሙሐመድ!!! إِنَّا كَفَيْنَاكَ الْمُسْتَهْزِئِينَ سورة الحجر 95 ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል፡፡ ሱረቱል ሒጅር 95 Indeed, We are sufficient for you against the mockers Surat Al-Hijr 96 በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው በሐቅና በባጢል መሐል የሚደረገው ትግል ከጥንት ከመጀመሪያው ሰው አደም(ዐለይሂ ሰላም) ዘመን ጀምሮ አላህ ምድርንና በላይዋ ያለውን እስከሚወርስበት ቀን(እለተ-ቂያም) ድረስ የሚቀጥል ነው፡፡ ባጢል ሁሌም ተሸናፊ ነው (አል-ኢስራእ 81)፡፡ ኢስላም ሃይማኖታዊ አስተምህሮው ግልጽ መሆኑ፣ በአላህና በባሮቹ መሐከል ቢያንስ በቀን አምስት ጊዜ በጸሎት እንዲገናኙ ማድረጉ፣ ዘርና ጾታ፡ ስልጣንና እውቀት በማለት በተከታዮቹ መካከል ምንም ልዩነት ሳያደርግ ሁሉንም በእኩልነት ማቀፉ የጠላትን ልብ ካደማ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ አሁንም እያደማ ነው፡፡ እነዚህ የኢስላም ጠላቶች ሙስሊሙን በሃይማኖታዊ ውይይት መርታት ሲያቅታቸው፡ ከፋፍሎ ለማጣላት ያደረጉት ሙከራ የተፈለገውን ያህል አልሳካ ሲላቸው፡ አሁን ደግሞ መጥፊያቸው በተቃረበበት ዘመን በነቢያችን(ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም) መጡብን፡፡ አግባብ ያልሆነ ምስል በመስራት የሳቸውን ክብር ለማጉደፍ ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡ የሳቸው ክብር አላህ ዘንድ መሆኑን ዘንግተውት ነውን? የሳቸው ክብር በሙስሊሞች ልብ መሆኑን ዘንግተውት ነውን? የሳቸውን ታላቅነት እንኳን ጤናማ አእምሮ ያለው ሰው ይቅርና ግዑዝ የሆነው ፍጥረት(የእሁድ ተራራ) እንኳ ያውቃል፡፡ እኛም ለሳቸው ያለንን ክብር ለመግለጽና ማንነታቸውን ለሰዎች ለመግለጽ የቻልነውን ያህል እንሞክር፡፡ ለዛሬ እሳቸው የእዝነት ነቢይ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃዎችን እንመለከታለን፡- 1. የእዝነት ነቢይ ናቸው فَبِمَا رَحْمَةٍ مِنَ اللَّهِ لِنْتَ لَهُمْ وَلَوْ كُنْتَ فَظًّا غَلِيظَ الْقَلْبِ لَانْفَضُّوا مِنْ حَوْلِكَ فَاعْفُ عَنْهُمْ وَاسْتَغْفِرْ لَهُمْ وَشَاوِرْهُمْ فِي الْأَمْرِ فَإِذَا عَزَمْتَ فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَوَكِّلِينَ سورة آل عمران 159 ከአላህም በሆነች ችሮታ ለዘብክላቸዉ። ዐመለ መጥፎ ልበ ደረቅም በሆንክ ኖሮ ከዙርያህ በተበተኑ ነበር። ከነርሱም ይቅር በል። ለነርሱም ምሕረት ለምንላቸዉ። በነገሩም ሁሉ አማክራቸዉ። ቁርጥ ሐሳብም ባደረግህ ጊዜ በአላህ ላይ ተመካ። አላህ በራሱ ላይ ተመኪዮችን ይወዳልና (ሱረቱ አለ-ዒምራን 159)፡፡ So by mercy from Allah , [O Muhammad], you were lenient with them. And if you had been rude [in speech] and harsh in heart, they would have disbanded from about you. So pardon them and ask forgiveness for them and consult them in the matter. And when you have decided, then rely upon Allah . Indeed, Allah loves those who rely [upon Him]. surat Ali imran 159 وَمِنْهُمُ الَّذِينَ يُؤْذُونَ النَّبِيَّ وَيَقُولُونَ هُوَ أُذُنٌ قُلْ أُذُنُ خَيْرٍ لَكُمْ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَيُؤْمِنُ لِلْمُؤْمِنِينَ وَرَحْمَةٌ لِلَّذِينَ آمَنُوا مِنْكُمْ وَالَّذِينَ يُؤْذُونَ رَسُولَ اللَّهِ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ سورة التوبة 61 ከነሱም (ከመናፍቃን) እነዚያ ነቢዩን የሚያሰቃዩ እርሱም ጆሮ ነዉ (ወሬ ሰሚ ነዉ) የሚሉ አልሉ፤ በላቸው ፦ ለናንተ የበጎ (ወሬ) ሰሚ ነው፤ በአላህ ያምናል ምእምናንንም ያምናቸዋል ከናንተም ዉስጥ ለነዚያ ላመኑት እዝነት ነዉ፤ እነዚያም የአላህን መልክተኛ የሚያሰቃዩ ለነሱ አሳሚሚ ቅጣት አላቸው። (ሱረቱ-ተውባህ 61)፡፡ And among them are those who abuse the Prophet and say, He is an ear. Say, [It is] an ear of goodness for you that believes in Allah and believes the believers and [is] a mercy to those who believe among you. And those who abuse the Messenger of Allah - for them is a painful punishment. surat At-Tawbah 61 لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِنْ أَنْفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُمْ بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَحِيمٌ سورة التوبة 128 ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በርሱ ላይ ጥኑ የሆነ፣ በናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን ርኅሩህ አዛኝ የሆነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ። (ሱረቱ-ተውባህ 128)፡፡ There has certainly come to you a Messenger from among yourselves. Grievous to him is what you suffer; [he is] concerned over you and to the believers is kind and merciful. Surat At-Tawbah 128 وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا رَحْمَةً لِلْعَالَمِينَ سورة الأنبياء 107 (ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም። (ሱረቱል አንቢያእ 107)፡፡ And We have not sent you, [O Muhammad], except as a mercy to the worlds. Surat Al-Anbiya 107 النَّبِيُّ أَوْلَى بِالْمُؤْمِنِينَ مِنْ أَنْفُسِهِمْ وَأَزْوَاجُهُ أُمَّهَاتُهُمْ... سورة الأحزاب 6 ነቢዩ፣ በምእምናን ከነፍሶቻቸው ይበልጥ ተገቢ ነው፤ ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው… (ሱረቱል አሕዛብ 6)፡፡ The Prophet is more worthy of the believers than themselves, and his wives are [in the position of] their mothers… Surat Al-Ahzab 6 አላህ ሆይ ያንተን አምላክነትና የረሱልን ነቢይነት ሳያውቁ ቀርተው ከሆነ ወደ እውነቱ መንገድ ምራቸው፡፡ አውቀው ጠመው ከሆነ በዚሁ ዱንያ ውርደታቸውን አሳየን፡፡ አሚን Click and Like ➤➤ https://facebook/Ustaz.Abuhyder
Posted on: Thu, 15 Jan 2015 23:41:29 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015