ወይ ማማ ጦቢያ! ስንቱን እንከፍ - TopicsExpress



          

ወይ ማማ ጦቢያ! ስንቱን እንከፍ ተሸክመሽዋል እቴ,,,እምምም ሰዉ ሀሳቡን በነጻነት የማይገልጽበት ፌስ ቡክ ላይ ዱቅ ብለን ከኛም ተብሶ ደግሞ እኛ አዳማጭ፣የሌላዉን ሀሳብ እንደ ሀሳብ የምናከብር፣ ከሆይ ሆይታ የነጻን ፍርደ ቀናዎች የሆንን ይመስል. . . ድምጻችን ተሰረቀ፣ ምርጫችን ተጭበረበረ፣ ፒሪሪም ፓራራም እያልን ለሀሳብ ነጻነት የምንሟገት እንመስላለን,,,, አሃ! እንዴት ነዉ ነገሩ እኔ ማንም ማንም ላይ በተንኮል ሲሸርብም ሆነ ሊቀድም ሲሽቀዳደም አላየሁም,,,ያየሁት ያለይሉኝታ በነጻነት ሀሳቡን ሲገልጽ ነዉ፡፡ካለፉት ድብብቆሾቻችን ወተን በነጻነት ሀሳባችንን ስንገልጥ ነዉ፡፡ ያልጣመንን አልጣመንም፣የጣፈጠንን ይደገመን ስንል፡፡ አለቀ፡፡ ይሄ ደግሞ ላወቀበት ማደግ፣ ብሎም ሀሳብን በቀናነት የሚያንሸራሽሩበት፣ ከስህተት የሚስተማሩበት አሊያም በሀሳብ ልዩነት ተሳስመዉ የሚለያዩበት እንጂ ጎረቤት እስኪረበሽ፣ከተኛንበት ደንቁረን እስክንወጣ ድረስ ያዙኝ ልቀቁኝ በሚል ቡራ ከረዩ የሚባባሉበት አልነበረም,,,,ኧረ ግድ የላችሁም አታካብዱት ሁሉንም ነገር፡፡ አሃ!ወይ አትንጫጩ ድምጻችሁን ቀነስ አድርጉልና!! ፍቅር ይስጠን አቦ! ይቺም እርስት ሆና. . .!!
Posted on: Tue, 01 Oct 2013 11:49:06 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015