የዓረና የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ቶርቸር - TopicsExpress



          

የዓረና የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ቶርቸር ተደረገ --------------------------------------------------- ጓዶች የዉቅሮ ስብሰባ ሪፖርት ሳላቀርብ ጠፋሁ። የውቅሮ ከተማ የዓረና ቅስቀሳና የህወሓቶች ምላሽ የሚገርም ነበር። እኛ በደንብ ቀሰቀስን። የዉቅሮ ህዝብ የህወሓትን አገዛዝ እንዳንገሸገሸው ተረዳን። የኛ ቅስቀሳ ሲጠናቀቅ ህወሓቶች የራስቸው ቅስቀሳ ጀመሩ። የመለስ ራእይ... እያሉ እንደተለመደው መዘመር ጀመሩ። (በሚቀጥለው ምርጫ የሚጠቀሙት ቅስቀሳ የመለስ ራእይ የሚል መሆኑ ከወዲሁ ማወቅ ችለናል)። ወደ ማታ አከባቢም ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ ህዝብ በዓረና ስብሰባ እንዳይሳተፍ፣ እያንዳንዱን ወላጅ ልጆቹ ወደ ስብሰባው እንዳይሄዱ መምከር እንዳለበት ካልሆነ ግን መንግስት እንደካደ ይቆጠርና በመንግስት እርምጃ እንደሚወሰድበት ያስፈራሩት ገቡ። ቅዳሜ ጠዋት (የስብሰባው ቀን) ሁሉም የዉቅሮ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች የስብሰባው አደራሽ በር ላይ ተገኝተው ወደ ስብሰባው የሚገባ ሰው መከልከል ጀመሩ። የነሱ መከልከል ያልበገረው ሰው ደግሞ ፎቶ ማንሳት ጀመሩ። የቀበሌ ሰራተኞች ህዝብ የቀበሌያቸው ሰው መቆጣጠር ያዙ። ሲገርመን እኛ ደግሞ እነዚህ ህዝብ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ፎቶ ማንሳት ጀመርን። (ካድሬዎቹ ፎቶ እንዳናነሳቸው ይፈሩ ነበር)። አንዱ ሲከለክል አይቼው ፎቶ አነሳሁት። ተናዶ ወደኔ እየሮጠ መጣ። ለምን ያለፍቃዴ ፎቶ ታነሳኛለህ? አለኝ። አንተስ ለምን ህዝብ ያለፍቃዱ በስበሰባ እንዳይሳተፍ ታደርጋለህ? አልኩት። እኔኮ ፀጥታ የማስከብር ፖሊስ ነኝ ብሎ መታወቅያውን አሳየኝ። ይገርማል ። ስሙ ተክላይ ይባላል። የዉቅሮ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ነው። ታድያ ፖሊስ ከሆንክ ለምን ፎቶ መነሳቱ አስፈራህ? ሕጋዊ ስራ እየሰራህ ከሆነ ለምን ትፈራለህ? አልኩት። ለመግባት የመጣ ሰው የኛ ንትርክ ለመስማት ከበበን። ፖሊስ አዛዡ (ሲቪል የለበሰ ነው) ዞር በሉ ብሉ በተናቸው። እንዲህ እንዲህ እያለ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ሆነ (ስብሰባው መጀመር የነበረብት 2:30 ነበር)። እኛ በገቡ ሰዎች ስብሰባውን ለመጀመር ወደ አደራሹ ገባን። ከጭቅጭቁ በኋላ ዞምቢዎቹ ሰው በቀጥታ ከመከልከል ወደ በዝምታ መከታተልና በቪድዮ ካሜራ መቅረፅ ተሸጋገሩ። ስበሰባው ተጀመረ። ህወሓቶች ገብተን ተሰብሳቢውን እንቀርፃለን አሉ። በስሰባው የነበሩ ወጣቶች ህወሓቶች እኛን ለመጉዳት ነው የሚቀርፁት፤ ስለዚህ አስወጡልን አሉን። ፖሊስ እንዲወጡ አደረገ። ካድሬዎቹ ከፖሊስ ተጋጩ። ካድሬዎቹና የኛ ሦስት ሰዎች እየተከራከሩ ፖሊስ ጣብያ ዋሉ። እንዲህ ሁኖ ሰብሰባው በሦስት ሰዓት ተጀምሮ በስምንት ሰዓት በጥሩ መንፈስ ተጠናቀቀ። የህዝብ ብዛት ግን አነስተኛ ነበር። በነበረው መንፈስ መሰረት በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ጠብቀን ነበር (ካድሬዎቹ ባይከለክሉት ማለት ነው)። የመጣ ግን በመቶዎች የሚቆጠር ነበር። እንዲህ ሁኖም ጥሩ ነው። መልእክታችን በሁሉ ቦታ ደርሷል። ያልሰማ የለም ማለት ይቻላል። ህወሓቶች ፈሪዎች ናቸው። አቶ ገብሩ አስራት ኢህአዴጎች በግለሰብ አስተያየት የሚደነግጡ ናቸው ብሎ ነበር። እዉነት ነው። ህወሓቶች ደንግጠው የዉቅሮ ከተማ በየካቲት 11 እንኳ የማይደረግ ቅስቀሳ ጀምረዋል። ዛሬ እሁድ ህዝብ ለሰለማዊ ሰልፍ እንዲወጣ አስገድደው ሰልፍ ጠርተው ነበር። ሰለማዊ ሰልፍ አይፈቀድም እያሉ ራሳቸው ሰለማዊ ሰልፍ ይጠራሉ። በጣም መደንገጣቸው መበስበሳቸው ያሳያል። ሰብሰባው አጠናቀን ወደ መቐለ ጉዞ ጀመርን። ስብሰባው ይመሩ ከነበሩ የዓረና አመራር አባላት አንዱ የዉቅሮ ከተማ (አጉላዕ) ተወላጅ የሆነና በ2002ዓም ዓረና ወክሎ የፓርላማ ተወዳዳሪ የነበረ መምህር ይልማ ኩኖም ነበር። እኛ ወደ መቐለ ጉዞ ስንጀምር እሱ ቤተሰቡ ለመጠየቅ ዉቅሮ ቀረ። የህወሓት ፖሊሶች ተከታትለው ያዙት። ስልኩን ነጠቁት። በፖሊስ መኪና ወደ መቐለ ይዘዉት መጥተው ቶርቸው ሲፈፅሙበት አደሩ። አለን የሚሉት የመግረፍት እርምጃ ካደረሱበት በኋላ አሁን ለቀቁት። መምህር ይልማ ኩኖም የዓረና ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የዉቅሮ ከተማ ተወዳዳሪያችን ነው። ለ24 ሰዓት ቶርቸር የሚፈፅሙ አምባገነኖች ያልታገልን ለማን ልንታገል ነው? የሚፈፅሙት ቶርቸር ደርጋዉያን ይፈፅሙት ከነበረ የከፋ ነው። It is so!!!
Posted on: Sun, 27 Oct 2013 16:20:50 +0000

Trending Topics



-left:0px; min-height:30px;"> Husband: aaj khane mein kya banaogi? Wife: Jo aap kaho H: Dal
Lunch Specials for Thursday September 12, 2013 Soups Du

Recently Viewed Topics




© 2015