#ABU_DAWD_OSMAN በፌስቡክ ድህረ ገፆች ላይ - TopicsExpress



          

#ABU_DAWD_OSMAN በፌስቡክ ድህረ ገፆች ላይ የሼህ ኑሩ ልጅ በማዕከላዊ እስር ቤት ቶርች እየተደረገ ነው ተብሎ የሚናፈሰው ዜና ከእውነት የራቀ አሉባልታ እና ቅጥፈት መሆኑ ተረጋጧል:: በፌስቡክ የማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ የሼህ ኑሩ ልጅ አባቴን የገደለው መንግስት ነው ብሎ በመናገሩ በማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ እየተደበደበ እንደሚገኝ የሚናፈሰው ዜና ከእውነት የራቀ እና መሰረተ ቢስ ዜና መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ ሆን ተብሎ የፌስቡክን መረጃዎች ተአማኒነት ለማሳጣት በሚል በመንግስት ካድሬዎች አዳዲስ አካውንቶችን በመክፈት የዚህን መሰሉ አሉባልታን በማናፈስ ላይ ይገኛሉ፡፡ የፌስቡክ ተጠቃሚውም በአዳዲስ የፌስቡክ አካውንቶች ካድሬዎቹ የለቀቁትን መረጃ ባለማወቅ መረጃውን እየተቀባበለው በመንግስት ካድሬዎች የተፈለገውን አላማ አንዲሰሰካለቸው ምክንያት ሆኗል፡፡በዚህም መረጃ መሰረት የሼህ ኑሩ ልጅ በማዕከላዊ በአሁኑ ሰአት ታስሮ ቶርች እየተደረገ እንደሆነ በማስመሰል ወሬ ያሶሩ ሲሆን በተረጋገጠው እውነታ መሰረት ግን የሼህ ኑሩ ልጅ በደሴ ከተማ በሰላም እየኖረ እንገሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከሼህ ኑሩ ልጆች መካከል ብቸኛው ወንድ ልጃቸው በአቋም ደረጃ ከህዝበ ሙስሊሙ ቢለይም የፅንፈኝነት ምልክት እና ጥላቻ የማያንፀባርቅ ሲሆን ሴት ልጆቻቸው ግን አባታቸው በመንግስት ከተገደለባቸው ጊዜ ጀምሮ ከበፊቱ በባሰ መልኩ በሙስሊሙ ላይ መርዛማ የሆነ ጥላቻ እንዳደረባቸው ታውቋል፡፤ ሴት ልጆቻቸው በተለየም በኢቲቪ "ሼህ ኑሩን ማን ገደላቸው" በሚለው ድራማ ላይ ከጅዳ ከተማ እንደመጣች ተገልፆ አስተያየቷን ስትሰጥ የነበረችው የሼህ ኑሩ ሴት ልጅ የቤቷ ደጃፍ ላይ በመቆም በበራቸው በኩል የሚያልፉ ኢስላማዊ መገለፃዎች የሚታይባቸውን እና ሱና ተከታይ ወንዶችን እንዲሁም ኒቃብ፣ጅልባብ እና አባያ የሚለብሱ ሴቶችን እናንተ የአባቴ ገዳዬች,እናንተ የአረብ ቅጥረኞች ለገንዘብ ብላችሁ አባታችንን ገደላችሁብን፣አባቴ በገንዘብ አልገዛ ሲላችሁ ገድላችሁት እናንተ በሰላም አትኗሯትም የሚሉ ዛቻና ስድቦችን እንደሚሰነዝሩ የአይን ምስክሮች ገልፀዋል፡፡ በተለየም በጉዳዩ ጋር እጃቸው አለ በሚል በሃሰት በደሴ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙትን የአንድ ቤተሰብ አባላቶችን ወደ ስራ ቦታቸው ድረስ በመሄድ የንብረት ጥፋት በተደጋጋሚ የሼህ ኑሩ ሴት ልጅ እንዳደረሰችባቸው ተዘግቧል፡፡ ይህንንም በማስመልከት ቤተሰቡ ለፖሊስ ቢያመለክትም ፖሊስ በበኩሉ አባታቸው ስለተገደለባቸው ተጎጂዎች ናቸው እና ታገሱ የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሼህ ኑሩ ወንድ ልጅ ግን ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር በአቋም ያባቱን ሃሳብ ደጋፊ ቢሆንም ተከባብሮ እና በለዘብተኛነት ጥሩ ግንኙነት እንዳለው ተዘግቧል፡፡ አባቱንም ገድለዋል በሚል በሃሰት የተወነጀሉትም ሙስሊሞች የሰፈሩ ልጆች እና ጉደኞቹም መሆናቸውም ተሰምቷል፡፡ በፌስቡክ የሚቀርቡ መረጃዎችን ተዓማኒነት ለማሳጣት የመንግስት ካድሬዎች ሆን ብለው የተሳሰተ መረጃዎችን በፌስቡክ ላይ በመልቀቅ ሙስሊሙን ለማሳሳት እና በሰዉ ዘንድ ሁሉም መረጃዎች ውሸት ናቸው ብሎ እንዲጠራጠር ለማስደረግ ከፍተኛ አንቅስቃሴ እያደረጉ ስለሚገኙ የሚለቀቁ መረጃዎችም በተለይም የዚህን መሰሉ ጥንቃቄ ሊወሰድበት የሚገባ መረጃዎችን በጥልቀት ሳናጣራ ከካድሬዎቹ እንደወረደ ተቀብለን ከማስተላለፍ መቆጠብ ይኖርብናል፡፡ ብልጦች አይደለንም ብልጣ ብልጦችም አያታልሉንም!!! ድል ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች!!! አላሁ አክበር!! To get more information like this page https://facebook/abudawdosman https://facebook/abudawdosman
Posted on: Thu, 03 Oct 2013 20:41:40 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015