An Icelandic Power Company is Negotiating with the Ethiopian - TopicsExpress



          

An Icelandic Power Company is Negotiating with the Ethiopian Government ... See at ... diretu.be/963892 | የአይስላንድ ኩባንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ድርድር ጀመረ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጂኦተርማል አንድ ሺሕ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ከመንግሥት ጋር ውል የገባው የአይስላንድ ኩባንያ ራይካጃቪክ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ድርድር ጀመረ፡፡ ድርድሩ ሚያዝያ 23 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡ ድርድሩ እየተካሄደ የሚገኘው በኩባንያውና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ ባለሙያዎች መሆኑ ታውቋል፡፡ የኩባንያው ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት ድርድሩ የኃይል ሽያጭ፣ ታሪፍ፣ ዋስትናና የውጭ ምንዛሪ ምጣኔን ያጠቃልላል፡፡ ‹‹ወደ ግንባታ ከመሸጋገራችን በፊት እነዚህ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ምላሽ ማግኘት አለባቸው፤›› ሲሉ የኩባንያው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የሚካሄደው ድርድር ሰፊ በመሆኑ ድርድሩ እስከ ክረምቱ ወራት ሊዘልቅ እንደሚችል የሚናገሩት እነዚህ ምንጮች፣ በመስከረም ወር 2007 ዓ.ም. ግንባታውን ለመጀመር የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን ወደ ሥፍራው ማንቀሳቀስ ይጀመራል ብለዋል፡፡ ይህ ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኩባንያ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ አካባቢ በሚገኘው ኮርቤቴ አካባቢ ከሚገኘው ጂኦተርማል በአራት ቢሊዮን ዶላር ወጪ አንድ ሺሕ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ለማመንጨት በመስከረም 2000 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ማድረጉ በማስታወስ የዘገበው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው፡፡
Posted on: Sun, 04 May 2014 10:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015