BY #Behredin Inqor Silent ከምንወዳቸው እና - TopicsExpress



          

BY #Behredin Inqor Silent ከምንወዳቸው እና ከምንናፍቃቸው ውድ ኮሚቴዎቻችንን እና ወንድሞቻችንን የተላከ መልዕክት !!! ፍትህ ብርቅ የሆነባችሁ ውድ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች የአላህ ሰላምና እዝነት በናንተ ላይ ይውረድ ፡፡ ፍትህን ፈልገው ከኛ ጋር ሲጮሁ የነበሩ ዑስታዞቻችንንና ወንድሞቻችን ዛሬ በእስር ላይ ቢሆኑም ለኛ የሚናፍቀንን አስተመሮታቸውን ፣ ምክራቸውን ወደኛ ከማድረስ አልተቆጠቡም፡፡ እንሆ ሰምተው (አንብበው) ከሚጠቀሙት ያድርገን፡፡ እነሆ የኮሚቴዎቻችንን ሰብሳቢ ከሆነው ኡስታዝ አቡበክር አህመድ (አቡኪ) መልዕክት እንጀምር፡፡ አቡበክር አህመድ ‹‹ እኛ የተከሰስንበት ክስ በኢትዮጲያ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የሚገኝ ክስ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ አይደለም እስካሁን በእስር ላይ የቆየንባቸው ጊዜያች ለናንተ ረጅም ጊዜ ቢመስላችሁም እኛ ግን ስምንት ቀንም የታሰርን አልመሰለንም፡፡ ምክንያቱም የታሰርነው ለኢስላም በመሆኑ ቀኑንም አናውቀውም፡፡ አሁንም ቢሆን እኛ እየከፈልን ያለው ነገር ትንሽ መሰዋትነትን ነው፡፡ እኛም ያገኘነውን ትልቅ ነስር ማንም አያገኘውም፡፡ እኛንም ታስረዋል ብላችሁ ለደቂቃም ቢሆን እንዳታስቡ፡፡ እናንተ ብቻ በርቱልን ፤ አንድነታችሁን ጠብቁልን፡፡ ጠንክራችሁ ታገሉ ሰላማዊ ትግሉንም ምንጊዜም ቢሆን እጅግ አሰልቺና ፅናትን የሚጠይቅ በመሆኑ ሳትሰለቹና ሳታክቱ ጠንክራቸሁ ትግላችሁን ሰላማዊነቱን በጠበቀ መልኩ ከምንጊዜውም በላይ አጠናክራችሁ ቀጥሉ›› ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡ ካሚል ሸምሱ ‹‹ መንግስት የተያያዘው ዘመቻ የሙስሊሙን ዑማ እንድነትን የመከፋፈልና የመበታተን ዘመቻ ስለሆነ ከምን ጊዜውም በላይ አንድነታችሁን አጠንክራችሁና አጥብቃችሁ መያዝ አለባችሁ፡፡ ›› ብሎም መልዕክቱን አስተላልፏል በድሩ ሁሴን ‹‹ ሁሉም ሰው በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ኢስላምን የመጠበቅ ሀላፊነት አለበት ፡፡ ተማሪው በትምህረቱ ፤ ነጋዴው በንግዱ መበርታትና መጠንከር አለበት፡፡ አሁን እኛ ላይ እየደረስ ያለው ጭቆናው ፣ በደሉ ፣ መከራውም ፣ ስቃዩም አሁሉም ነገር ማለት ይቻላል ሱና ነው፡፡ ስለዚህም አብሽሩ እናንተም መበርታት ያለባችሁ ነገር ላይ ሰደቃን ማብዛት ፤ ቁርዓን በመቅራት መስጂድ ውስጥ ያሉ ደርሶችን ማብዛት ፤ መሰጂዶችን መጠበቅ እንዳለበን አንድነታቸንን ጠብቀን መሄድ መጠንከር፡፡ እኛንም በዱዓ አትርሱን›› በሎዋል አህመዲን ጀበል ‹‹ ወድ የኢስላም ልጆች ሁላችሁም የኢስላምን አጥር በምንም አይነት መልኩ እንዳይደፈር ዘብ ቁሙ !!! ሁላችሁም የኢስላም ጠባቂ ዘቦች ናችሁ፡፡ አንድ ጠንዚዛ ትልቅ ግንድ ለመሰርሰር ሲሞክር ‹‹አትልፋ መቼም አይሳካልህም›› ይሉታል፡፡ ጥንዚዛውም መልሶ ‹‹ የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ›› ግንዱን አሰረስራለሁ በማለት መለሰ፡፡ ምንም ጊዜ ቢፈጅ ድሉ የኢስላም ነው፡፡ እናንተም በአንድነታችሁ ፀንታችሁ ትግሉን አጠንክራችሁ በመያዝና እስልምናን በመጠበቅ ሀላፊነታችሁን ልትወጡ ይተበቅባችሁዋል›› በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡ ኑሩ ቱርኪ ‹‹ በመስሊሙ ውስጥ ሙስሊም መስሎ ሙስሊሙን አሳላፈው ለጨቋኞችና ለበዳዮች የሚሰጡትን ጠላቶቻችሁን ለይታችሁ በማውጣት ከማህበራዊ ነገሮች ማራው፤ ኸይር ስራዎችን ማብዛት ፤ ሱና ፆሞች ላይም መበርታት ፤ ሰላተል ለይልም መቆም ፤ ዱዓ ማብዛት፤ ወጣቶችም መስጂድ ውስጥ በማብዛት መስጂዶችን ከሴረኞች መከላከልና መቆጣተር፡፡ በመጨረሻም ወደ ዩንቨርስቲ የሚሄዱ ተማሪዎችን የአቀባበል ፕሮግራም ላይ የሚሰጡ አስተምሮቶችን የሚሰጡ ልብ ብሎ መከታተልና ከሚሰጠው ትምህርት የሚጠቅም ከሆነ መቀበል ካልሆነ መተው ይኖርበችወል፡፡ በሀገሪቱ ወደሚገኙ ዩንቨርስቲዎች ከሄዳችሁም በኋላ ትምህርታችሁ ላይ ጠንክራችሁ በመማር ዲኑንም የመጠበቅ ሀላፊነታችሁን አጠንክራችሁ ያዙ፡፡ እስልምናን ለመከፋፈል የተጀመረውን ዘመቻ በአላህ ፍቃድ ከሽፏል በአንድነታችሁም ፀንታችሁ ቀጥሉ›› በማለት መልዕክቱን አስተላልፏ፡፡ ውድ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ሆይ የተላለፈልን መልዕክቶች ሰምተው አንብበው ከማየተገበሩት እንዳንሆን፡፡ ሁላቸንንም የሚመለከት ጉዳይ ነው በላያችን ላይ የተጋረጠብን፡፡ ሕፃን አዋቂ ብለን የምንለየው አጀንዳ አይደለም፡፡ ጠላቶቻችን በዲናችን ላይ ነው ድንበር ያለፉብን፡፡ በስራችን አይደለም ፤ በቤተሰባችን ይደለም ፤ በመኖሪያ ቤታችን አይደለም፤ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለተፈነከቱለት ፣ ቢላል በጠራራ ፀሀይ ድንጋይ ለተጫነበት ፣ አማር እናትና አባቱን አይኑ እያየ በሞት ላጣበት ዲነል ኢስላም ነው፡ አሁንም የምናየው ያንን ያለፉ የሰሃቦች ታሪክ ነው፡፡ ኮሚቴዎቻችንና ውድ ወንድሞቻችን ለዲናቸው አለን በማለታቸው አስር ቤት ለእስር ቤት እየተሸከረከሩ የሚገኙት ለኢስላም ነው፡፡ ሁላችንም የነርሱን አርዐያ ተከትለን ለዲኛችን መቆም ይኖርብናል፡፡ ምክራቸውን በልባችን አንግበን ዲናችን ላይ የመጣውን ፈተና በአንድነት ልንጋፈጠው ይገባል፡፡
Posted on: Wed, 02 Oct 2013 07:33:59 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015