Belgu Kasa Amara Force ከመተከል አውራጃ - TopicsExpress



          

Belgu Kasa Amara Force ከመተከል አውራጃ ተፈናቅለው የነበሩና የተመለሱ አማራወች እየተደበደቡ ነው። በቤኒሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በልዩ ልዩ ቀበሌዎች የተፈናቀሉ አማራዎች አሁንም ችግር ላይ መሆናቸው ከስፍራው በደረሰን መረጃ መሰረት ማረጋገጥ ችለናል። ግንቦት 15 ቀን ወደ ቦታው የተላከው የኢትዮ ምህዳር ዘጋቢ የነበረ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ሁኔታውን አጣርቶ ለመመለስ ሲሞክር በአካባቢው ፓሊስ ተይዞ ከአንድ ሳምንት በኋላ አሶሳ በክልሉ ፕሬዘዳንት በተጻፈ ደብዳቤ መለቀቁ የሚታወስ ሲሆን ተፈናቃዮቹ ለጋዜጠኛው መረጃ ሰጥታችኋል በሚል ሰበብ በተደጋጋሚ ይደበደባሉ፣ ልዩ ልዩ ጥቃቶችም ይደርስባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በወረዳው የባሮዳ ቀበሌ የብአዴን አስተባባሪ የሆነው አቶ ሻምበል በለው የተባለው ግለሰብ ከዚህም በፊት እራሱን ነጻ በማውጣት አማራዎቹን ያፈናቀለ እና አሁንም በጥቃቱ ከፍተኛው ተዋናይ መሆኑን ተጎጅዎች ይናገራሉ፡፡ ይኸው ግለሰብ ሀምሌ 21 ቀን 2005 ዓ.ም. በግምት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በርካታ የአካባቢውን ነዋሪዎች በማስተባበር ዘጠኝ ግለሰሰቦች ቤት ሰብረው በመግባት ስማችንና የአካባቢያችን ገጽታ አጥፍታችኋል፣ ለጋዜጠኛ መረጃ ሰጥታችኋል፤ በማለት ተደብድበዋል፡፡ ከዘጠኙ ከተደበደቡ ሰዎች መካከል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሶስቱ ተጎጅዎች ወደ አማራ ክልል ጃግኒ ከተማ መጥተው በግል ክሊኒኮች እየታከሙ መሆናቸውን አስታማሚዎች በስልክ አረጋግጠውልናል፡፡ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው ቻግኒ ከተማ ከታከሙት ግለሰቦች መካከል 1. በለጠ መንግስቴ 2. ጥላሁን ገበየሁ 3. አቸነፍ ወንዴ ይገኙበታል፡፡ በወረዳው ከ5200 በላይ ግለሰቦች መፈናቀላቸው የሚታወስ ሲሆን እስከአሁን ሁሉም ሙሉ በሙሉ ወደ ነበሩበት አልተመለሱም፡፡ የሄዱትም በስበብ አስባቡ ችግር ላይ እንደሆኑ ለመረዳት ተችላል፡፡ ይህ ጊዜን እያሳለሰ የሚደረግ በአንድ ብሄር ላይ ብቻ ያነጣጠረ ጥቃት መንግስት በአስቸኳይ ማስቆም ካልቻለ አገሪቱንም ለከፋ ችግር ሊጋርጣት ይችላል፡፡
Posted on: Thu, 01 Aug 2013 18:46:11 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015