City Administration gives eviction orders to resident for LRDP - TopicsExpress



          

City Administration gives eviction orders to resident for LRDP ...See at ... diretu.be/356788 |በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎ ነዋሪዎች በአስቸኳይ እንዲነሱ ትእዛዝ መተላለፉ ተገለጸ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በካሳንችስ፣ አሜሪካ ግቢ እና ተክለሃይማኖት አካባቢ የሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎች የሚኖሩበትን የመኖሪያ ቤት እና አካባቢ በ20 ቀናት ወስጥ እንዲለቁ ትእዛዝ ማስተላለፉን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል ፡፡ የከተማው አስተዳደር ውሳኔውን ያስተላለፈው በመልሶ ማልማት ፕሮግራም ምክንያት እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ አስተዳደሩ አስቸኳይ ትእዛዝ ካስተላለፈባቸው አካባቢዎች መካከል ልደታ አካባቢ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፣ የአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት አካባቢ ፣ቂርቆስ አካባቢ እዲሁም የደጃች ውቤ አካባቢዎች ይገኙበታል፡፡ በተላለፈው ውሳኔ መሰረት የተማው አስተዳደር 1200 ሄክታር መሬት ለመልሶ ማልማት ለማግኘት አቅዶ ሆኑን የተጠቆመ ሲሆን 40 ሄክታር የሚሆነው መሬት በቀጥታ ለባለሃብቶች እን ደሚሰጥ ተገልቷል፡፡ የተያዘው የበጀት ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት በካሳንቺስ አካባቢ ከኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል እስከ ዮርዳኖስ ሆቴል ፤ ከባምቢስ ሱፐርማርኬት እስከ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን 26 ሄክታር መሬት ለመልሶ ማልማት ዝግጁ ለመድረግ ማሰቡንም ዘገባው አመልክቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ የአዲስ አበባ የመሬት ልማት እና የመልሶ ማልማት ኤጀንሲ ምክትል ስራ አስከያጅ አቶ ግርማ ብርሃኑን ጠቅሶ ዘገባው እንዳመለከተው ለልማት ተነሺዎች የተዘጃቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ሙሉ በሙሉ ያለመጠናቀቅ ለመልሶ ግንባታው አፈጻጸም ተግዳሮት ሆኖ መቆየቱን ዘግቧል፡፡
Posted on: Sat, 26 Apr 2014 16:00:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015