Egypts President Elect al-Sisi ready to visit Ethiopia for water - TopicsExpress



          

Egypts President Elect al-Sisi ready to visit Ethiopia for water talks - የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ በአባይ ወንዝ ዙሪያ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፡፡ ቅዳሜ ዕለት የግብጽ መንግስት ሚዲያ ከሆነው ዕለታዊው አል አህራም ጋር ባደረጉ ቃለ ምልልስ፣ “ውይይት እና መግባባት ችግሩን ለመፍታት ሁነኛ መፍትሄ ናቸው፡፡ ከየትኛውም አካል ጋር ወደ ግጭትና ጠላትነት ከማምራት ይልቅ የሚሻለውም ይህ ነው፤ የግብጽን ጥቅም የሚያስጠብቅ ከሆነ ኢትዮጵያ ሄጄ ለመወያየት ፍቃደኛ ነኝ ለሀገሬና ለውሃ መብቷ መጠበቅ የትኛውንም ጥረት ከማድረግ ወደኋላ አልልም ጉዳዩ የሞት ሽረት ጉዳይ ነውና” ብለዋል፡፡ More...diretu.be/759555
Posted on: Sun, 18 May 2014 18:30:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015