Eritrean refugees in Ethiopia vow to join armed struggle ... See - TopicsExpress



          

Eritrean refugees in Ethiopia vow to join armed struggle ... See at .... diretu.be/777994 | በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች የኤርትራን መንግስት በትጥቅ ትግል ከስልጣን ለማውረድ ተዘጋጅተናል አሉ በሺዎች የሚቆጠሩ በኢትዮጵያ የስደተኛ መጠለያ ካምፖች የሚገኙ ኤርትራዎን የኤርትራ መንግስትን ከስልጣን ለማስወገድ ትጥቅ በማንገብ የትጥቅ ትግል ከሚያደርጉ የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚዎቸ ጋር እንደሚቀላቀሉ መናገራቸውን ሱዳን ተሪቢዩን ዘግቧል፡፡ የኤርትራዊያኑ ስደተኞች ውሳኔ ኤርትራ የ23ተኛ ዓመት የነጻነት በዓሏን እያከበረች ባለችበት ወቅት የተላላፈ ነው፡፡ ዘገባው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ ሀገሪቱ ነጻነቷን ካገኘችበት ግዜ ጀምሮ በአንድ ፓርቲ ስርአት የምትመራ እና ከዓለማችን ጨቋኝ የመንግስት ስርአቶች ውስት አንዷ እንድትሆን አድርገዋል ብሏል፡፡ ኤርትራዊኑ ስደተኞች ለሱዳን ትሪቢዩን በላኩት መግለጫ የአስመራ መንግስት በሀገሪቱ ዲሞክራሲን ማስፈን ካለመቻሉ በተጨማሪ በሰብአዊ መብቶች አያያዝ እና በህዝቦች ነጻት ላይ ከፍተኛ ጫና ስለሚደረግ በመንግስት ስልጣን ላይ መቆየት የለበትም ብለዋል፡፡ ‹‹እዚህ ቁጭ ብለን ተአምር ከመጠበቅ የኤርትራን መንግስት ለመጣል ትጥቅ እናነሳለን›› ብለዋል ኤርትራዊኑ ስደተኞች በመግለጫቸው፡፡ See at .... diretu.be/777994
Posted on: Fri, 23 May 2014 12:00:00 +0000

Recently Viewed Topics




© 2015