#EthioMuslims ምስጋና የሚገባው ህዝብ! ሐሙስ - TopicsExpress



          

#EthioMuslims ምስጋና የሚገባው ህዝብ! ሐሙስ መስከረም 9/2006 ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ወገቡን አጥብቆ ለሀይማኖታዊ መብቱ ሰላማዊ ትግል ውስጥ ከገባ ይኸው ሁለት አመት ሊሞላው እየተንደረደረ ነው፡፡ ሁለት የፈተና፣ የመከራ፣ የትግል፣ የበደል፣ ከምንም በላይ ደግሞ የሞራል ልእልና እና የበላይነት የተጎናጸፈበት አመታት ናቸው - የድልም! በዚህ ወቅት ውስጥ ይህ ድንቅ ትውልድ የታዩበት ባህርያት ዛሬ ለምስጋና ብእር እንድንነሳ አስገደደን፡፡ ለዚህ ህዝባችን ምስጋና በቂ ሆኖ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የሚመሰገንበት ውለታው ብዙ ነው፡፡ ጀዛው አላህ ዘንድ ነው፡፡ ግና መልካም ባህሪዎቹን እየጠቀሱ ጎልተው እንዲወጡ ማድረጉ ታሪካችንን ቀርጾ በማስቀመጡ ረገድ የሚጫወተው ሚና ይኖረዋል፡፡ ህዝባችን መልካም ባህሪዎቹን አውቆ እንዲያሳድጋቸው፣ እንዲያዳብራቸውም ያግዛል፡፡ ከመልካም ባህሪያቱ ንጻሬ ኋላ ደግሞ ድክመቶቹን ተመልክቶ በቻለው እንዲቀርፋቸው በር ይከፍታል፡፡ አንድ አንድ እያልን አብረን እያየናቸው አንድነትን የመረጠ ህዝብ! በትግላችን ውስጥ ጎልተው ከወጡ ህዝባዊ ባህርያት አንዱና ዋነኛው አንድነቱ ነው፡፡ የአህባሽ አደጋ ሙስሊሙን እንዲሰነጣጥቅ ታስቦ የመጣ ነበር፤ ግና የአላህ ፍላጎት ተቃራኒው ሆነና ጠንካራ የአንድነት መሰረት ይኖረን ዘንድ ተቻለ፡፡ ህዝባችን ለዚህ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ የአላህ ስጦታ የሆነው አንድነት መሰረቱ ከበፊቱ ጠንክሮ ይጣል ዘንድ ቀልቡን ለውህደት ከፍቷል፡፡ ጭቅጭቅና ልዩነት ከሚፈጥሩ አጀንዳዎች በተቻለው በመራቅ በፍጹም መተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ወንድማዊ ግንኙነት ፈጥሯል፡፡ መጅሊሱና ጸብ የመፍጠር አባዜ የያዛቸው አመራሮቹ በአንድነቱ ላይ የሚያደርጉትን ትንኮሳ በብስለት ዝቅ ብሎ አሳልፏል፡፡ አንድነቱን ለመበተን ያላደረጉት ጥረት፣ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፤ ግና አልቻሉም! ባለፉት ሁለት መውሊዶች በሙስሊሙ መካከል ክፍተት ለመፍጠርና ትግሉን ለማኮላሸት ያልተደረገ ጥረት አልነበረም፡፡ ሕዝቡ ግን ‹‹መውሊድ አይከፋፍለንም›› ሲል አሳፈራቸው፡፡ በተወዳጁ ነቢይ ስም ሙስሊሞችን መነጣጠል እንደማይሳካላቸው አረጋገጠላቸው፡፡ ‹‹ወሐቢያ፣ ሱፊያ›› የሚሉ ስሞች በፓርላማ ጭምር ሲነሱ ሙስሊሙ ግን አንድነትን መርጦ ‹‹እኛ ሙስሊሞች ነን›› አላቸው፡፡ አልሐምዱሊላህ! አንድነታችንን ዘላቂና የጠለቀ ያደርግልን ዘንድ አላህን እንለምነዋለን! ለዚህ ድንቅ ባህሪውም ህዝባችንን እናመሰግናለን! አላሁ አክበር! Like ☑ Comment ☑ Share ☑ ይሄን ሊንክ ጠቅ አድርገው ይከተሉና አዲሱ ገጻችንን ላይክ ያድረጉ! https://facebook/DimtsachinYisema2
Posted on: Thu, 19 Sep 2013 06:10:10 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015