Ethiopia Warns Withdrawing Supporting Abyei Peacekeeping Mission - TopicsExpress



          

Ethiopia Warns Withdrawing Supporting Abyei Peacekeeping Mission ... See at ... diretu.be/482385 | ኢትዮጵያ በአቢዬ ከሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ኃይል ራሴን አገልላለሁ ስትል አስጠነቀቀች፡፡ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን የይገባኛል ጥያቄ ባስነሱባትና የነዳጅ ሀብት እንዳላት በሚታወቀው በአቢዬ አካባቢ ከሌሎች ሀገራት ሰራዊት ጋር በጥምረት የኢትዮጵያ ሰራዊት ሰላም በማስከበር ላይ እንደተሰማራ ይታወሳል፡፡ ሱዳን ትሪብዩን አንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውስጥ ሪፖርትን ጠቅሶ እንደጻፈው ኢትዮጵያ ሁለቱ ጸበኛ ወገኖች ልዩነቶቻቸውን በመፍታት ቦታውን በሙሉ ኃላፊነት ካልተረከቡ የወታደሮቿን የቦታው ላይ ቆይታ ጉዳይ ዳግም እንደምታጠናው መግለጿን ጠቅሶ ጽፏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በነገው ዕለት የቦታውን የሰላም ማስከበር ግዳጅ የጊዜ ገደብ ለማደስ አሊያም ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ሀሳብ ለማጽደቅ እንደሚሰበሰብ ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚለው የሰላም ማስከበሩ ግዳጅ ሲጀመር ሁለቱ ጥለኛ ሀገራት የገቡትን ቃል ባለማክበራቸው የሰላም ማስከበሩን ሂደት አዳጋች አድርጎታል፡፡ ለዝርዝሩ ....diretu.be/482385
Posted on: Mon, 19 May 2014 04:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015