Ethiopia to Sell 100MW Electric Power to Yemen | ኢትዮጵያ - TopicsExpress



          

Ethiopia to Sell 100MW Electric Power to Yemen | ኢትዮጵያ ለየመን 100 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ልትሸጥ መሆኑ ተሰማ፡፡ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ለኬንያ 100 ሜጋዋት፣ ለጅቡቲ 50 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ሀይል እንደሸጠች የሚታወቅ ሲሆን፣ ለሱዳን ደግሞ 200 ሜጋ ዋት ለመሸጥ ተስማምተው እስካሁን 100 ሜጋዋት እየሸጠች እንዳለች ታውቋል፡፡ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል ለመግዛት አራተኛዋ ሀገር የምትሆነው ደግሞ የመን ስትሆን በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ሁለቱ ሀገራት እያካሄዱ ያሉት ድርድር ተጠናቅቆ በቅርቡ ኢትዮጵያ ለየመን ለአንድ ዓመት 100 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ለመሸጥ የሚያስችል ውል እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል፡፡ የኤሌክትሪክ መስመሩ በቀይ ባህር ወለል ስር እንደሚዘረጋ የታወቀ ሲሆን ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ሁለቱ ሀገራት እንደሚያፈላልጉ ተነግሯል፡፡ ዝርዝሩን ➤➤➤ diretu.be/383462
Posted on: Sun, 26 Jan 2014 12:36:12 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015