Ethiopian Opposition Activists Bailed After Poll-Protest Arrests | - TopicsExpress



          

Ethiopian Opposition Activists Bailed After Poll-Protest Arrests | Read More at.....goo.gl/WQsLWo | በፖሊስ ተይዘው የነበሩ የተቃዋሚ አባላት በዋስ መለቀቃቸው ተነገረ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች ስምንት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አዘጋጅተው በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የፓርቲውን መሪ ጨምሮ በፖሊስ ተይዘው የነበሩ ሌሎች ወደ 80 የሚጠጉ ተቃዋሚዎች በዋስ መለቀቃቸውን ብሉምርግ በዘገባው ያስነብበናል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲን ህዝብ ግንኙነት ሀላፊን ጠቅሶ ብሉምበርግ እንደዘገበው የፓርቲው መሪ አቶ ይልቃል ጌትነት ከታሰሩት መካከል ሲሆኑ ሌሎች የአራት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት እስካሁን በእስር ላይ ናቸው፡፡ ህዝብ ግንኙነቱ አክለውም ምንአልባትም እስካሁን በእስር ላይ የሚገኙት ለምርመራ አንተባበርም በማለታቸው ይሆናል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በህገመንግስቱ መሰረት በግንቦት ወር ሀገራዊ ምርጫ የምታካሂድ ቢሆንም ህግን ምክንያት በማድረግ የተቃዋሚዎች ሰብዓዊ መብቶች እየተከበሩ አይደለም ሲል አምንስቲ ኢንተርናሽናልን ጠቅሶ ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ…
Posted on: Fri, 12 Dec 2014 13:30:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015