Gebru Kahsay Kiflu August 29 ኣሸንዳ የሴቶች - TopicsExpress



          

Gebru Kahsay Kiflu August 29 ኣሸንዳ የሴቶች ዲሞክራሲያዊ ፀጋ “ኩሎን ኣዋልዲሃ ለሄዋ በምግበረ ሰናይ እለ ተሰርግዋ እሞንዋመ ሃኬት እለ ፅሕዋ ዕበያተኪ ዜንዋ ተፈስሂ ማርያም ሓዳሰዩ ጣዕዋ” መፅሐፈ ሰዓታት በገብሩ ካሕሳይ ኣሸንዳ ኢትዮጵያ ብቻ ከምታከብራቸዉ ልዩ (Endemic) ከሆኑ በሰፊው ትዕይንተ ህዝብ ከሚከበሩ እንደነ መስቀል ፣ጨምበላላ ፣ዕሬቻ ፣ጥምቀት ወዘተ የሃይማኖት ቅልቅል ይኑራቸዉ ኣይኑራቸዉ የባህል ኣብዮት (cultural revolution) ሊያውጁና ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ሊያስተዋዉቁ ከሚችሉ በዓላት ኣንዱ ነዉ ። ኣሸንዳ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ እንዲሁም ደግሞ ለትግራይ ክልል ኣጎራባች ከሆኑ የኣማራ ክልል ወረዳዎች የሚከበር ሲሆን በተለይ የትግራይ ክልል ርእሰ ከተማ በሆነችዉ መቀሌ በደማቅ ስነ ስርዓት ይከበራል። ኣሸንዳ መከበር የሚጀምረው ፆመ ፍልሰታ መፈፀሙን ተከትሎ የቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት ለማብሰር ምክንያት በማድረግ ነዉ። ኣሸንዳ ስያሜው ያገኘዉም በክረምት ወራት ከሚበቅለዉ ሃመልማል (ኣረንጋዴ ቅጠል)ነዉ። ይህ ስያሜ ሊያገኝ የቻለውም ልጃ ገረዶች በዓሉን ሲያከብሩ ኣረንጋዴ ቅጠሉን ከወገባቸው ታጥቀው ዉበት ተከናንበዉ እየተወዛወዙና እየዘለሉ ሲጫወቱ ዉበት ከሚሰጣቸው አሸንዳ ከሚባል ቅጠልነዉ። ኣሸንዳ ልዩ ከሚያደርጉበት ኣንድ ነገር ደግሞ ሌሎቹ በዓላት ፆታን ሳይለዩ የሚከበሩ ሲሆኑ ኣሸንዳ ግን ለየት ባለ መልኩ በሴቶች ብቻ የሚከበር መሆኑ እና የሴቶች ክብርና የመናገር ነፃነትም ከሌላ ግዜ በተለየ መልኩ መብት የሚያጎናፅፍ በዓል መሆኑ ነዉ። የኣሸንዳ ታሪካዊ ደራ ኣሸንዳ መቼና የት ቦታ መከበር እንደጀመረ በውል የሚታወቅ ባይኖርም ስለኣከባበር ሁነታውና ኣንድምታዉ ግን ሁለት ኣስተያየቶች ኣሉ። ኣንደኛውና በስፋት ተቀባይነት ያለው ስለ ኣሸንዳ ኣመጣጥ ሃይማኖታዊ ይዘት ያለዉ ሲሆን ይህ ደግሞ በኦርቶዶክስ ሊቃውንት ቤተ ክርስትያን ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እየተተረከ የመጣ ኣስተያየት ነዉ። ሁለተኛዉ ደግሞ በቅርቡ የትናሱ ኣዳንድ የባህል ኣጥኚዎች በዓሉ ምንም ዓይነት ሃይማኖታዊ ኣመጣጥ እንደሌለዉ የሚገልፁ ናቸዉ። እንደ ኦርቶደክስ ሊቀውንተ ቤተ ክርስትያን ኣተራረክ ኣሸንዳ መክበር የተጀመረዉ በኦሪት ዘመን ሲሆን ቦታዉ ደግሞ በሃገረ እስራኤል ነዉ። በኦሪት ዘመን ሴቶች ተሰባስበዉ ቤተ እግዚኣብሔር ሄደው ምስጋናቸው ያቀርቡ ነበር ከዛ መልስ ደግሞ ንጉሳቸዉን ያመሰግኑ ነበርይላሉ። በተጨማሪም ደግሞ ንጉስ ዮፍታሄ ጦርነት ለመዝመት ባሰበበት ግዜ ጠላቱን ኣሸንፎ ሲመለስ ፊት ለፊት ያገኘዉን ነገር ለአምላኩ እንሚሰዋለት ቃል ገብቶ ነበር። እንደ ኣጋጣሚ ነገር ሆኖ ንጉሱ ጦርነቱ ድል ኣድርጎ ሲመለስ ፊት ለፊቱ ያገኘዉ ነገር ደግሞ ልጁ ነበረች። ንጉሱ በጣም ተጨነቀ ልጁን እንዴት መስዋዕት እንደሚያደርግም በሃሳብ ተዋጠ። ልጁም የኣባትዋ ሃሳብና ጭንቀት ለማወቅ ኣባትዋ ጠየቀች ። እሱም ስዕለት እንደተሳለና የሆነዉም ነገር እስዋላይ እንደ ሆነ እያዘነና እየተጨነቀ ነገራት ። ልጁቹም ኣባቷ በተፈጠረው ነገር ማዘን እንደሌለበትና ቃሉ ማጠፍ እንደማይኖርበት ነገረቸው ። ቢሆንም መስዋዕት ከመሆንዋ በፊት ትንሽ ግዜ እንዲሰጣትና ከጓደኞችዋ በመሆን ልጅነቷ ለማጣጣም ለሁለት ወራት እንድትጫወት እንዲፈቅድላት ለመንቸዉ። ፈቀደላትም የድንግልናዋ ወራት ልጅነቷዋ ከጋደቾችዋ በመሆን ከተጫወተች በኃላም መስዋዕት ለመሆን ሄደች ይላሉ። እንደ ሊቃውንቶቹ ኣገላለፅ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ በህገ ልቦና፣ በህገ ኦሪት በኃላም በህገ ወንጌል ያለፈች በመሆንዋ ያን ውርስ ይዛ የንጉስ ዮፍታሄ ልጅ ለማሰብ በድንግልናቸውና በልጅነታቸዉ ግዜ ልጅነታቸዉ ለማጣጣም ይጫወታሉ። በሌላ መልኩ ደግሞ በኦሪት ዘመን ሴቶች በጣም የተበደሉና የተጨቆኑ ነበሩ ይላሉ ። በርግጥ የወንድ የበላይነት ኣስካሁን የዘለቀ ቢሆንም ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድሓኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መውለድዋን ተከትሎ በከፊልሞ ቢሆን በደሉንና ጭቆናዉን መቃለሉ ያስረዳሉ ። በኦሪት ግዜ ሴት ልጆች በወንዶች ብእጅጉ ይበደሉ ነበር ። ምክንያቱም እንደ ወንዶች ኣስተሳሰብ ሄዋን ተሳስታ ባሏ ኣዳምን ኣሳስታ ዕፀ በለሱን እንደባላቸዉና ከገነት እንደወጣቸዉ ከዛም ያሰዉ ልጅ በሄዋን ( በሴት) ስህተት ምክንያት ከገነት ወጥቶ ምድረ ፍዳ ለመኖር እንደተፈረደበት ምክንያት በማድረግ ሴቶች ሲበደሉና ሲጨቆኑ ኖሮዋል ይላሉ ። ቀደም ብሎ እንደገለፀዉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መድሃኒት መዉለድዋ ግን ሴቶች ነፃነታቸዉ እንዲያዉጁ በር ከፍቶላቸዋል ይላሉ ። ከዚህ ግዜ ጀምሮ እመቤታችን የሴቶች መመክያ እንደሆነች ደግሞ ይናገራሉ። በዕለት ሓሙስ የሚነበበዉ ኣምስተኛዉ የዉዳሴ ማርያም ክፍልም ኣባ ኤፍሬም ሶርያዊ እንዲህ ሲል ይገልፃታል ። “ትምክህተ ኩልነ ድንግል ማርያም ወላዲተ ኣምላክ ዘበእንቲኣሃ ተስዕረ ዘቀዳማዊ መርገም እንተሃደረት ዲበ ዘመድነ በዕልወት ዘገበረት ብዕሲት በልዓት እምዕፅ በዕንተ ሄዋን ተዓፀወ ሆህተ ገነት ወበዕንተ ማርያም ድንግል ተርህወለነ”። ይህ ምክንያት በማድረግ ደግሞ ሴቶች መመከያቸዉን የሆነች ቅድስት ድንግል ማርያም ለማክበር ሲሉ ድሮ ሰያከብሩት ያነበሩት ኣሸንዳ በስዋ ዕርገት ዓመታዊ በዓልም ሆነ እንዲቀጥል ኣድረጉት ይላሉ ። ሊቀውንተ ቤተ ክርስትያንም 16 ቀናት (ሁለት ሳምንት) በሚፀመው የፍልሰታ ፆም በሳዓታትና በማህሌት እዲሁም በቅዳሴ ለድንግል ማርያም ክብር ቀናና ሌሊት ምስጋናቸዉ ያቀርባሉ። በሰዓታት ኣንዱ በሆነዉ ከሎሙ በሚባል ክፍልም “ኩሎን ኣዋልዲሃ ለሄዋ በምግበረ ሰናይ እለ ተሰርግዋ እሞንዋመ ሃኬት እለ ፅሕዋ ዕበያተኪ ዜንዋ ተፈስሂ ማርያም ሓዳሰዩ ጣዕዋ” እያሉ ኣባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የደረሰውን ውዳሴ ያዜማሉ። ፆመ ፍልሰታ መፈፀሙን ተከትሎ የቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት ለማበሰርም ደናግል ሴቶች ተሰባስበዉ መጀመርያ ወደ ቨቤተክርስትያን ያመራሉ ። በቤተክርስትያን ቅፅር ዉስጥም “ማርያም ዋይ ፀሓየ መፂአለኹ ዛመፅብዓ” እያሉ ከዓመት ዓመት መሸጋገራቸውንያ፣በሂወት መቆየታቸውና ኣሸንዳን ስላደረሳቸዉ ምስጋናቸውን ያቀርባሉ። ኣሸንዳ ሊያልቅ ኣንድ ቀን ሲቀረዉም የቄስን ስም በመጥራት የጨወታውን ግዜ በመጠናቀቁ በማዘን “ኣቦ ቃሺየ ዳንዩና ዕምበብ ዓዳ ኸይዳ ሳኣን ዋና” እያሉ ይደመድማሉ። ሁለተኛውን ስለ ኣሸንዳ ኣመጣጥ የሚሰጠው መላምት ዳግሞ ከኣንዳንድ የባህል ኣጥኚዎች የሚቀርብ ሓተታ ነዉ ። እንደነዚህ ኣጥኚዎች ኣባባል ኣሸንዳ ባህላዊ በዓል ሲሆን የበቀለውም እዚሁ በሰሜን ኢትዮጵያ በጥታዊቷ ኣክሱም ነዉ ። ኣሸንዳ ባህላዊ በዓል ለመሆኑ የሚያቀርቡት ምክንያት ደግሞ ለምን እንደነ ጥምቀትና መስቀል ታቦታት ወጥተው በሰፊው ትዕይንተ ህዝብ ከካህናት ጋር ኣይከበርም ለምንስ ሃይማኖታዊ ይዘት ካለው በሌላ ዓለም ኣይከበርም ቢያንስ በኣርቶዶክስ ተከታይ ሃገራት ለምን በትግራይና በኣማራ ኣንዳንድ ወረዳዎች ተወስኖ ቀረ ይላሉ ። ነግር ግን ታቦታት ወጥተዉ ከማይከበርባቸዉ በዓላት ውስጥ ኣሸንዳ ብቻ ኣይደለም ። በትንሳኤ፣ ልደት ወዘተ ታቦት ኣይወጡም። ጥምቀትና መስቀል ቦታቦት ታጅበዉ መከበር የተፈለገዉም በሚታይ ቦታ ተግባራዊ በሆነ መልኩ ለማክበር ስለሚያመቹ ነዉ ። ስለዚህ ጥያቄያቸዉ ጥንካሬ ያጣል ማለት ነዉ። ሌላዉ የሚያነሱት ጥያቄ ደግሞ ለመን ለኛ የሆነዉ ሁሉ ከሌላዉ ዓለም የመጣ አስመስለን እናቀርባለን ነዉ።ጥያቄያቸው ተገቢ ቢሆንም ኣሸንዳ ከሌላ ዓለም መጣ የሚያስብለው ኣንድምታ የለውም ። ቀደም ብሎ እንደተገለፀዉ ኢትዮጵያ ከሌሎች በተለየ መልኩ በህገልቦና ፣በህገኦሪትና በህገ ወንጌል ፀንጥታ የኖረች ኣገር ነች። ስለዚህ ሌሎች ሃገራት ኣሸንዳ ቀርቶ ጥምቀትና መስቀል እንኳን የማክበር ባህል የላቸውም ። ኣብዛኞቹ ሃገራትም የኦሪት እምነት ያልነበራቸውና ክርስትና ዕምነት ዘግይተው የተቀበሉ ናቸዉ ። እንዲህ ኣይነት መላምትም ከኣንዳንድ የባህል ኣጥኚዎችና በዓሉን የሁሉ (secular) ለማድረግ ከሚፈልጉት የመንግስት ኣካላት በስተቀር በህዝብና በሊቃውንተ ቤተ ክርስትያን ተቀባይነት የለዉም ። ኣሸንዳ ባህላዊ ይሁን ሃይማኖታዊ በዓል፣ከኦርቶዶክስ ውጪ የሆኑ ሌሎች ሰዎች ያክብሩት ኣያክብሩት ፣የት ይጀመር መቼ በተወሰኑ ቦታዎች ይወሰን ኣይወሰን ፀጋዎቹ ብዙ ናቸዉ። ሴቶችን የሚያጉናፅፋቸው ሃሴት ልዩና የማይቆይ መብት ተወዳጅ ነዉ ። ሃገራዊ ፋይዳ ኣለዉ ። ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያ ጠቀሜታው የጎላ ነዉ ። የኣሸንዳ ፀጋዎች ነሓሴ 16 የዛሬ ዓመት እያርገዉና በትግራይ ሴቶች በጉጉት ከሚጠበቁ ቀናት ኣንዱ ነዉ ። ነሓሴ 16 የኣሸንዳ በአል የሚጀመርበት ቀን ነዉ ። የትግራይ ሴቶች የማንነት፣የነፃነት ፣የሃሴት፣የልጅገረድነት፣የህፃንነት መግለጫ ነዉ። ልጀገረዶች ደስታቸዉን የሚገልፁበት፣የሚዝናኑበት፣ኣንደበታቸዉ የሚከፍቱበት፣ኣፍ ኣዉጥተዉ የሚወቀሰውን የሚወቅሱበት፣ ሲያሻቸውም የሚያሞጉሱበት ኣሸንዳ። ኣሸንዳ ለትግራይ ሴቶች የህፃንነት መብታቸውን የሚያከብር፣የሴትነት ነፃነታቸውንም የሚያጎናፅፍ በዓል ነዉ ። የህፃናትና የሴቶች መብት የተከበረበት ቀን ቢኖር የኣሸንዳ ሰሞን ነዉ። እንደሚተታወቀው የኢትዮጵያ ህፃናት መብታቸዉ እምብዛም አይከበርም። ያለ ዕደሜያቸዉ ከትምህርት ገበታቸዉ ተስጓጉለዉ ኣቅማቸው የማይፈቅደው ስራ ይሰራሉ ፣ከብት ይጠብቃሉ፣የመናገር መብትቸው ይከለከላሉ ወዘተ። በኣሸንዳ ሰሙን ግን እነዚህ ነገሮች የሉም። ሴቶችን መሰራት ፣ከጨወታ መከልከል፣የሚፈልጉትን ከማድረግ ማገድ ማሕበረሰብ እንደማሕበረሰብ ፀያፍ ነዉ ።እንደሻቸዉ እንዲዘሉ ፣እንዲዝናኑ፣እንዲለብሱ እንዲናገሩ ይደረጋል በኣሸንዳ። በጉጉት የሚጠብቅዋት ኣሸንዳ በኣረንጋዴ ቅጠል ኣሸብርቀው፣ በጌጣጌጥና በኩል ተውበው ባህላዊ ልብስ ተከናንበዉ “ኣሸንዳዋይ ናዓሚ ናዓሚየ ተጋኒና ሎሚየ” እያሉ ለኣሸንዳ ያላቸዉን ክብርና ናፍቆት ይገልፃሉ። ሴቶች በኣሸንዳ ሰሙን የሚወቅሰዉን ይወቅሳሉ የሚወደሰዉን ያሞግሳሉ። የሚገርመዉ ነገር በጋዜጣኝነት ስም ማጥፋት (defamation) የምንለዉ ነገርም እንኳን በኣሸንዳ ሰሙን ፈፅሞ ኣይሰራም። የኣሸንዳ ልጆች እንዳሻቸዉ ቢሳደቡ ስሜን ኣጠፋችብኝ ተብሎ መክሰስ የለም ። መክሰስ ቀርቶ መልስ መስጠትም ነውር ነዉ ፣ያዋርዳል። የኣሸንዳ ልጆች የፈለጉትን ጠይቀዉት ኣልሰጥ ያላቸዉ ሰው እንዲህ በማለት ይሰድቡታል ለወንድ፦ ዓመት ዓቒርዎ ኣምስ ሓሪምዎ ወይ ዝገጣጢ ሽሮ ረሲዕዎ ድሮ ለሴት፦ “እንጣጢዕ ቡቕላ ማይ ስዋኣየ ኣደንጎር ባሕሪ መጠቕኣየ ለዚኣዶሰብ ትብልኣየ ።” በማለት የሴትነት ሙያ እንደሌላት ለመግለፅ እየተሳደቡ ይዘፍናሉ ። ኣዋረዱኝ ብሎ መልስ ለመስጠት ወይ ለመምታት የመኮረ ደግሞ እንዲህ ይሉታል። “ኣታዮ ጉደኛየ ጓልዶ ኣለዋ ዳኛየ” ። ያለዉን ሰጥቶ ኣክብሮ ለሸኛቸዉ ደግሞ እንዲህ እያሉ ያሞጉስታል ። የጋራ፦ ፈሰሰ ሃማይ ነሓሰ መኾምቡያ ለይለይየ ክብረት ይሃበለየ እያሉ ይሰናበታሉ ። ይህ የኣሸንዳ መወቃቀስና መወዳደስ ግን ኣሸንዳ ላይ ብቻ ተገድቦ መቅራት የለበትም ።የኣሸንዳ ባህል ብቻ መሆን ኣልነበረም ።ሁሌም ቢሆን በፐሎቲካዊ ጉዳዮችንም ብንለምደዉ መልካም ነገር ነዉ። ኣሸንዳ የሚሰጠዉና የሚፈጥረዉ ደስታም ልዩ ነዉ።እንኳን ለባለቤቱ ለልጅ ገረዶች ለተመልካችም ቀልብ ይስባል፣ ይመስጣል። ኣንድ ነገር ትዝ ኣለኝና ተማሪ በነበርኩበት መቐለ ዩኒቨርስቲ የሆንኩትን ልንገራችሁ። ክፍል ዉስጥ እየተማረን ( በኣጋጣሚ ዘግይተን ስለገባን ክረምት እዛዉ ነበርን መምህሩ ስልክ ተደለት ዉጭ ይወጣል ። እንደ ኣጋጣሚ ደግሞ የኣሸንዳ ልጆች መቐለ ዩኒቨርስቲ ግቢ ዉስጥ ገብተዉ ኣበባ መስለዉ እየዘለሉ ይጫወታሉ። እኔም መስኮት ከፍቼ እየመሰጠኝ እነሱም ስመለከት መምህሩ በሩ ከፍቶ ይገባል፣ ተደናግጬ ወደ መቀመጫየን ለመመለስ ስርበተበት ምን ሁነህ ነዉ ብሎ ይጠይቀኛል ። የተመለከትኩት ነገር በፍርሃት ነገርኩት ። የሱ መልስ ግን ይቆጣኛል ብየ ካሰብኩት በተቃራኒ ነበር ።ይልቁንም ኣይዞህ ዛሬ ደስ ሊልህ ይገባል። በዓመት ኣንድ ግዜ በሚሳቅበትና ደስታ በሚገኝበት ኣገር ይህ ተገኝቶ ደስታህን ብትገልፅ ደስ ይላል ኣለኝ። ኣዎ ልክ ነዉ በድህነት በምታውቀው ኣገር እንዲህ በህብረት ኣየወጡ ደስታ መግለፅ ኣእምሮን ከማደስ ኣልፎ ባህልን ያሳድጋል፣በጎገፅታህን ለዓለም ያሳዉቃል፣ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ይሰጣል ኣሸንዳ። ኣሁን ያሉ የኣከባበር ግድፈቶች ኣሸንዳ ከምን ግዜም በላይ ደምቆና ኣምሮ እንዲከበር መንግስት እና የተለያዩ ኣካላት ከቅርብ ግዜ ወዲህ ጥራት እያረጉ ነዉ ።ጥረታቸውንም ይደገፋል፣ የባህል ኣብዮት ለመፍጠር ፣በጎገፅታን ለመቀየር፣ዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ጠቅሜታ እንዲያመጣ ያግዛልና። ነገር ግን በጎ ከሆነ ጥረታቸዉ ጎን ለጎን ኣንዳእድ ኣለስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን እየተመለከትን ነዉ። ለምሳሌ መንግስት ኣሸንዳ በክፍተኛ ሁኔታ ደምቆ እንዲከበር እርሰበርስ ውድድር እንዲደረግ በየወረዳዎችና ቀበሌዎቹ ምልመላ ያደርጋል ።ይህ ምልመላ ግን የኣሸንዳ ትውፊትና እሴት በእጅጉ የሚፃረር ነዉ ። መልማዮቹ መስፈርታቸው የሚፈልጉትን ሰው ገንዘብ እንዲያገኝ መወጮ የከፈለ ፣ተሳትፎ ያለዉ እያሉ ከድሬ ኮድሬውን በዕድሜ ለኣሸንዳ የማይመጥን ከኣራት እስከ ኣምስት ልጆች የወለዱት ይመርጣሉ ።ይህም በጣም የኣሸንዳ ማንነት ይፃረራል ። ኣሸንዳ የደናግል ልጀገረዶች ተምሳሌት ነዉ ።፣ኣሸንዳ ገንዘብ ማግኛ ኣይደለም ። መፃሃፉ (መልክኣ ወዳሴ) “ደናግል በእንቲኣኪ ዘበጣ ከበሮ” ነዉ የሚለዉ። ደናግል ለንቺ ሲሉ ከበሮ ይመታሉ ፣ዜናሽን ይናገራሉ እንደማለት ነዉ። ይህ ነገር ግን በኔ ቀበሌ የታዘብኩት ብቻ ነዉ ። የሌለዉ መረጃ የለኝም ። መንግስት በኢቲቪ ማስታወቅያው ላይ ግን የዕድሜ ገደቡን ከ12 እስከ 14 የሚል ነው። በሌላ በኩል ደግሞ መንግስትና የተለያዩ ኣካላት ኣሸንዳን ደምቆ እንዲከበር የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ቢቀጥል መልካም ነዉ ።ነገር ግን እነዚህ ኣካላት ኣሸንዳን ካለው ፖለቲካዊ ሁኔታ መያያዝና መናገጃ ማድረግ የለባቸውም ። ምክንያቱም ኣሸንዳ የህዝብ፣ የልጅ ገረዶች ጥንታዊ መዓል ነዉ።ጥንታዊዉን ኣሸንዳ በማስተዋወቅ የቲሪዝም ሃብት ማድረግ ይቻላል። ነገር ግን ትውፊቱና እሴቱን ፈር በማይለቅ መልኩ መሆን ሲቻል ነዉ ። የደስታ ፣የባህል፣የመናገር ነፀነት፣የውበት፣ኣገራዊ የማንነት መገለጫ ልናደርገዉ ይገባል። ኸደት ኸደት ኣሸንዳ ዕምበብ ኸደት!! መልካም የኣሸንዳ በዓል‼ this was published in maraki magazin for ashenda.
Posted on: Tue, 08 Oct 2013 06:18:12 +0000

Trending Topics



class="stbody" style="min-height:30px;">
Thank you friends for yet an other wonderful year. This year we
Black Friday Deals + Northpoint Hotel Collection Therma Plush
WISDOM FOR LIVING A VICTORIOUS AND A SUCCESSFUL FAMILY LIFE.TO

Recently Viewed Topics




© 2015