Haile Gebrselassie Withdraws From Hamburg Marathon | ሀይሌ - TopicsExpress



          

Haile Gebrselassie Withdraws From Hamburg Marathon | ሀይሌ ገ/ስላሴ በሀምቡርግ ማራቶን እንደማይሮጥ ሲያስታውቅ ቀነኒሳ በቀለ እና ጥሩነሽ ዲባባ በማንቸስተር ይሮጣሉ በለንደን ማራቶን የሞ ፋራ አሯሯጭ የነበረው ሀይሌ ገ/ስላሴ በሀምቡርግ ማራቶን የፊታችን እሁድ ይሳተፋል ተብሎ ቢጠበቅም የመተንፈስ ችግር ስላጋጠመው በውድድሩ እንደማይሳተፍ አስታውቋል፣ በለንደን በአሯሯጭነት በተሳተፈበት ወቅት የለንደን አየር ስላልተመቸው ችግሩ እንደተነሳበትም አስታውቋል፡፡ ህመሙን ለማዳን ዋነኛ አስፈላጊው ነገር እረፍት ብቻ ነው ያለው ሀይሌ በዚህም ምክንያት ከውድድሩ እራሱን ማግለሉን አስታውቋል፣ በሌላ ዜና በፓሪስ ማራቶን የቦታው ሪከርድ ጭምር በመስበር ያሸነፈው ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን አሸናፊው ኬንያዊው ኪፕሳንግ ጋር በማንቸስተር ከሁለት ሳምንት በሁዋላ ሊገናኙ ነው፣ በማንቸስተር የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር ከቀነኒሳ በቀለ እና ኪፕሳንግ ውድድር በተጨማሪ የአለም እና የኦሎምፒክ የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊዋ ጥሩነሽ ዲባባ በሴቶቹ ምድብ የአምና ድሏን ለመድገም ትሮጣለች፡፡ በልምድ ማነስ በለንደን ማራቶን በኤደን ኪፕላጋት እና በፍሎረንስ ኪፕላጋት የተቀደመችው ጥሩነሽ ዲባባ ከ2008 ጀምሮ የ5ሺህ ሪከርድን በ14፡11፡15 በስሟ እንደተመዘገበ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የክረምቱ በሌሎች የበጋ ወቅት ከመግባቱ በፊት እና የትራክ ውድድር ከመጀመሩ በፊት የለንደን ውድድር ለሁሉም አትሌት መፈተኛ ነው፡፡ በትራክ የ10ሺህ ሜትር ምንም ሽንፈት ደርሶባቸው የማያውቀው ቀነኒሳ በቀለ እና ጥሩነሽ ዲባባ በለንደን የጎዳና ሩጫ መልካሙን ሁሉ ይግጠማቸው፡፡
Posted on: Tue, 29 Apr 2014 10:30:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015