Manchester United transfer rumours: Is Bastian Schweinsteiger a - TopicsExpress



          

Manchester United transfer rumours: Is Bastian Schweinsteiger a target for Louis van Gaal? ... See at ... diretu.be/799232 | የማንቸስተር ዩናይትድ የዝውውር ወሬዎች፡- ባስቲስ ሽዋንስታይገር የቫን ሀል ተመራጭ ሆነ ? ሁለት ሆላዳዊያን ለቫን ሀል አዲሱ የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሁለት የሆላንድ ብሄራዊ ቡድን አባላትን ለማንቸስተር ዩናይትድ መልምለዋል፣ ቫን ሀል የፈለጉዋቸው ሆላንዳዊያን የፌኖርዶቹን ጆርዲ ክላሲ እና የመሀል ተከላካዩን ቡሩኖ ማርቲንስን ነው፡፡ ቫን ሀል የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ መሆናቸውን ተጠቅመው ትልቁን የሆላንድ ቡድን ተጫዋቾች ለአዲሱ ክለባቸው በመመልመል ማበሳጨት አልፈለጉም እናም የአለም ዋንጫው ሲያበቃ ከፌኖርድ ጋር ለመደራደር አስበዋል፡፡ ፊል ጆንስ ከፔሩ ለሚደረገው ጨዋታ ዝግጁ መሆኑ ተነገረ የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ የሆነው ፊል ጆንስ ለአለም ዋንጫ እንደሚደርስ መረጃዎች እየወጡ ነው፣ የፊታችን አርብ እንግሊዝ ከፔሩ በምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ተሰልፎ ይጫወታል ተብሎ ቢጠበቅም ከጉዳት ገና ማገገሙ ስለሆነ የመሰለፉ ነገር አጠራጥሮአል፡፡ በዴቪድ ሞይስ ዘመን ልምምድ ላይ ጉዳት የገጠመው ጆንስ ለረጅም ጊዜ ከጉዳት ጋር ሲታገል ቆይቶአል፡፡ ሴስ ፋብሪሀስ በማንቸስተር አይፈለግም ሉዊስ ቫን ሀል የባርሴሎናውን ሴስ ፋብሪሀስ የማስፈረም ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላቸው አስታውቀዋል ሲል ዘ ሰን የተሰነው ጋዜጣ ዘግቦአል፣ የቀድሞው የአርሴናል ተጫዋች ለረጅም ጊዜ በማንቸስተር ዩናይትድ ሲፈለግ የቆየ ሲሆን አምና ለካታሎኑ ክለብ ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወቃል፡፡ ሆኖም ፋብሪጋስ በቫን ሀል ዝርዝር ውስጥ አልተካተተም፡፡ የባስቲን ሸዋን ስታይገር ቀጣይ ማረፊያው ማንቸስተር ዩናይትድ ይሆን እንደ አክስፐረስ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ የባየር ሙኒኩ ባስቲን ሸዋን ስታይገር በማንቸሰተሮች አይን ውስጥ ገብቶአል፣ የጀርመኑ ተጫዋች በአሊያንዝ አሬና ተቀዳሚ ተመራጭ መሆኑ አብቅቶአል፣ ጋረዲዮላ የሚመርጡት ቶኒ ክሮስና ቲጎን ነው፡፡ ስምምነቱ የሚፈጸም ከሆነ ቫን ሀል ከቀድሞ ክለባቸውን ተጫዋች ጋር ዳግም ይገናኛል፡፡ ቻው ቤቤ የፖርቹጋሉ የክንፍ ተጫዋች ቤቤ በስፖርተንግ ሊዝበን እየተፈለገ ነው፣ የ23 አመቱ በ2010 ወደ ማንቸስተር በ7 ሚሊየን ፓውንድ ከተዛወረ ጀምሮ ምን ተጽእኖ በማንቸስተር መፍጠር አልቻለም፣ እናም በውሰት ሰጥተውት ነበር እንደ ዴሊ ሜል ዘገባ ከሆነ በዛው በውሰት በሄደበት በቋሚነት ሊር እንደሚችል ጽፎአል፡፡
Posted on: Tue, 27 May 2014 11:00:00 +0000

Trending Topics



yle="min-height:30px;">
1. I am planning a 7 hour car trip with my ds in the new year. He
It took me about 45 minutes to get through the application process
Holiday Deals McKleinUSA WEST TOWN 15704 Brown Fly-Through
Nemesis One Motorworx Custom Painting, Body Kits & Body
Exploring Macroscopic Quantum Mechanics in Optomechanical Devices

Recently Viewed Topics




© 2015