More than twenty tones of Tantalum deposit found in Gudji Zone - - TopicsExpress



          

More than twenty tones of Tantalum deposit found in Gudji Zone - በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ከ20 ሺህ ቶን በላይ የታንታለም ማዕድን ክምችት ተገኘ፡፡ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቨይ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ታምሩ መርሻን ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘገበው የታንታለም ማዕድን በአገሪቱ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ቀንጢቻ አካባቢ በብዛት መኖሩ ተረጋግጧል፡፡ ዳይሬክተሩ አንደተናገሩት የታንታለም ሃብት ጥቅም ላይ ሲውል ለሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች፣ ለሞባይል መለዋወጫ ዕቃዎች እና ለተለያዩ የኢንዱስትሪ አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ የቻይና፣ የእስራኤልና የኢትዮጵያ ማእድን ልማት አክሲዮን ማህበር ጨምሮ ሰባት ኩባንያዎች በታንታለም ማእድን ፍለጋና ምርምር ፈቃድ የወሰዱ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን በማዕድን ዘርፍ ደግሞ ከ260 በላይ ኩባንያዎችና ባለሃብቶች ተሳታፊ ናቸው ተብሏል፡፡
Posted on: Mon, 14 Jul 2014 18:10:37 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015