My plan is to hit $10m mark by 2016 - Bethelehem Tilahun Alemu | - TopicsExpress



          

My plan is to hit $10m mark by 2016 - Bethelehem Tilahun Alemu | እ.አ.አ በ2004 አዲስ አበባ ውስጥ የተመሰረተው ‘ሶልሪቤልስ’ የተሰኘው የጫማ ማምረቻ ድርጅት መስራችና ባለቤት ቤተልሄም ጥላሁን፣ የድርጅቷን ገቢ እ.አ.አ በ2016 ወደ 10 ሚሊየን ዶላር የማሳደግ እቅድ እንዳላት ገለጸች፡፡ ተወልዳ ባደገችበት ዘነበወርቅ አካባቢ የሚገኙ የዕደ ጥበብ ክህሎት ያላቸውን በማሰባሰብ፣ ከባለቤቷና ከቅርብ ዘመዶቿ ባገኘችው መነሻ ካፒታል የዛሬ 8 ዓመት የመሰረተችው ድርጅት በአሁኑ ወቅት ከ100 በላይ በሚሆኑ ሰራተኞቹ የሚያመርታቸው ጫማዎች ከ30 በላይ በሚሆኑ ሀገሮች እየተሸጠ ይገኛል፡፡ በዓመት 1 ሚሊየን ዶላር ትርፍ የሚያስገባው የቤተልሄም ድርጅት ሊጋተም አፍሪካ በተባለው ታላቅ የኢንተርፕሪነርሺፕ ውድድር ላይ ለመጨረሻው ዙር ካለፉ 5 ድርጅቶች መሀልም አንዱ ሆኗል፡፡ ሙሉ ለሙሉ በሀገር በቀል ጥሬ ዕቃ ኢትዮጵያዊ የጫማ አሰራርን ከዘመናዊ ስልት ጋር በማዛመድ በእጅ የሚሰሩት የሶልሪቤልስ ጫማዎች በምርት ሂደቱ ምንም ዓይነት የካርበን ልቀት የሌለውና አካባቢን የማይበክል መሆኑ፣ በተለይ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በሚሰጠው የምዕራቡ ዓለም ሸማች ዘንድ ከፍተኛ ተፈላጊነትን አስገኝቶለታል፡፡ ከውጭ ሀገር የሚመጡ ጫማዎችን መጫማት እንደ ትልቅ የደረጃ መለኪያ በሚታይባት አዲስ አበባ ላይ ቤተልሄም ግን አለማቀፍ ተቀባይነት ያለው ኢትዮጵያዊ የጫማ ብራንድ የመፍጠር ራዕይ ይዛለች፡፡ የቤተልሄም የጫማ ማምረቻ ድርጅት ጫማዎቹን ታይዋን ውስጥ በከፈተው የመሸጫ መደብርና እንደ አማዞን እና ኢንድለስ ባሉ የኢንተርኔት የኤሌክትሮኒክስ የግብይት ድረ ገጾች እየሸጠ ያለ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ በካናዳ፣ ጣልያን፣ አውስትራሊያ፣ እስራኤል፣ ስፔን፣ ጃፓን እና አሜሪካ የፍራንቻይዝ የሽያጭ ስልት ጀምሯል፡፡ በስራዋ ትልቅ አለማቀፍ ዕውቅና የተቀዳጀችው ቤተልሄም ጥላሁን ባለፈው የፈርንጆቹ ዓመት መግቢያ ላይ በዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ላይ Young Global Leader በሚል ተመርጣለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ጊዜያት Most Outstanding Businesswoman እና Most Valuable Entrepreneur’ በሚል በተለያዩ ድርጅቶች ተመርጣለች፡፡ ለበለጠ ማብራሪያ ይህን ይጫኑ --> diretu.be/855272
Posted on: Sun, 03 Nov 2013 09:00:29 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015