New Study Reveals Ethiopian Customs & Revenue Authority Most - TopicsExpress



          

New Study Reveals Ethiopian Customs & Revenue Authority Most Corrupt ... See at ...diretu.be/324885 | የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ በለስልጣን ሙስና የተስፋፋበት መስሪያ ቤት መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ *የኤሌክትሪክ እና የቴሌኮም ዘርፎችም ሙስና ይስተዋልባቸዋል ተብሏል ሰላም የልማት አማካሪ JGAM በተባለ የተራድኦ ድርጅት እገዛ ከፌደራል የስነምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥናት የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ በለስልጣን በከፍተኛ ደረጃ ሙስና የተስፋፋበት ተቋም መሆኑን ይፋ አድርገዋል፡፡ ጥናቱ የኮንስትራክሽን ፈቃድ አሰጣጥ እና የመሬት አስተዳደርም ከባለስልጣኑ በመቀጠል ሙስና የተስፋፋባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡ ጥናቱ በሀገር ውስጥ የሚከወኑ የውጭ ኢንቨስትመንት እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የሙስና ተጋላጭነትን በመዳስ በሀገር ደረጃ በአጠቃላይ ደሰሳ ሙስና ቀንሷል ቢልም የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ፣ የመሬት ፣የኢንቨስትመንት ፈቃድ አሰጣጥ፣ የወጪ እና የገቢ ንግድ ፣ የውጭ ምንዛሪ ፣ ግብር እና ቀረጥ ፣ የኤሌክትሪከ እና ቴሌኮም እና የአገልግሎት ዘርፉ አሁንም ከፍተኛ የሙስና ተግባር የሚታይባቸው ናቸው ብሏል፡፡ የፌደራል የስነምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አሊ ሱሌማን በጥናቱ የተመከተው የሙስና ደረጃ ውጤት ቀድሞም ቢሆን በኮሚሽኑ የሚታወቅ መሆኑን ጠቅሰው የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን እና የማህበረሰባዊ የገንዘብ ተቋማት በኮሚሽኑ ትኩረት ተሰጥቶባቸው እየተሰራባቸው ያሉ እና ወደፊትም የምንቀጥልባቸው ናቸው ብለዋል፡፡ የጥናቱ አካል ከሆኑ እና ምለሽ ከሰጡ ኢንቨስተሮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢንቨስትመንት እና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ለተቋራጮች በሚሰጡበት ግዜ 24 በመቶው ተገቢ ያልሆኑ ክፍያዎች እንደሚፈጸምባቸው የጠቆሙ ሲሆን ጥናቱ በማጠቃለያው መንግስት አሁንም በጉዳዩ ላይ ትልቅ ትኩረት ከመስጠት ባለፈ አገልግሎት ሰጪ የመንግስት ሰራተኞችን ደምወዝ ማተካከል እንደሚገባው ጥቆማ ሰጥቷል፡፡ በጥናቱ 400 የሚሆኑ የውጭ ሃገራት ኢንቨስተሮች መሳተፋቸውም ተጠቁሟል፡፡
Posted on: Thu, 22 May 2014 20:00:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015