Nile Basin countries to negotiate Entebbe Agreement - DireTube | - TopicsExpress



          

Nile Basin countries to negotiate Entebbe Agreement - DireTube | የአባይ ተፋሰስ ትብብር ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሮች በኢንቴቤው የትብብር ስምምነት ላይ ማሻሻያ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ሊነጋገሩ ነው በሚል ዛሬ አንድ የግብፅ ሚዲያ አስነበበ። የታንዛኒያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ከአባይ ተፋሰስ ትብብር ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሮች ጋር በውሀ ክፍፍል ላይ ለመወያየት ከሁለት ወር በኃላ እቅድ መያዛቸውን አስታውቀዋል ይለናል ዘገባው፣ በተለይ በግብፅ ባለው የውሀ ፍላጎት መጨመር ጉዳይ ላይ አተኩረው ለመወያየት ፍላጎት እናዳላቸው አክለው ተናግረዋል። የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቃል አቀባይ ባድር አብደላቲ ታንዛኒያ ባቀረበችው መፍትሄ የሁሉንም የተፋሰሱን ሀገራት ፍላጎት አሟልቶ አንድ እርምጃ ሊያስኬድ ይችላል ብለዋል። ተጨማሪውን በግብፅ በኩል ያለውን ወቅታዊ አቋም ያንብቡ...diretu.be/859796
Posted on: Thu, 29 May 2014 05:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015