Olympic Official: Brazil’s Games ‘Really Are Not Ready in - TopicsExpress



          

Olympic Official: Brazil’s Games ‘Really Are Not Ready in Many, Many Ways’ | የአለም ዋንጫው ሊጀመር ከአራት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ብቻ ቀርቶታል የብራዚል ጣጣ ግን ገና አላለቀም ለሰባት አመትየተዘጋጀችበት የአለም ዋንጫ መስተንግዶ ብራዚልን ተጨማሪ ቀናት ሊያስጠይቃት ነው፣ በርካቶች አለም ዋንጫ በደቡብ አፍሪካ ሲካሄድ የዝግጅት መስተንግዶና ግንባታ ያልቃል ብለው ባይገምቱም ለአፍሪካ አለም ዋንጫን መስጠትን ባያምኑበትም ዝግጅቱ ግን አፍሪካን ያኮራ ሆኖ አልፎአል፡፡ አሁን በላቲን አሜሪካዋ የኳስ ሀገር ከብዙ ተቃውሞ ጋር የአለም ዋንጫን ለማስተናገድ ሽርጉድ ላይ የምትገኘው ብራዚል ውድድሩን የተሳካ ለማድረግ እያደረገችው ያለው ዝግጅት ጊዜው ደርሶ ያለ ስታዲየም እንዳይካሄድ ስጋት ተደቅኖባታል፡፡ ሀገራት የብሄራዊ ቡድናቸውን ስሞች ይፋ ማድረግ በጀመሩበት በዚህ ውድድሩ ሊጀመር አራት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ብቻ በቀረበት ወቅት ሶስት ውድድሩ የሚካሄድባቸው ስታዲየሞች ግንባታ አለማለቅ የኤሌክትሪክ ስራ ይሰራ የነበረ የ32 አመት ወጣት ህይወት ማለፍ ነገሮችን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎአቸዋል፡፡ ብራዚል እመኑኝ ስታዲየሞቹ ይደርሳሉ ብትልም ግንባታው ግን ስጋትን ፈጥሮአል፣ ሌብነቱ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ስጋት፣ በሪዮ የዝርፊያውን ቁጥር ለመቀነስ እና ከመላው አለም የሚመጡ ደጋፎዎችን ለማስተናገድ ልክ እንደ መልካም ነገር ሌቦችም ተዘጋጅተዋል፣ ቀምተው ለመሮጥ ይህ እንዳይሆን ግን የብራዚል ፓሊስ እና መከላከያ አዲስ ሀይል በማሰማራት የመንደር ለመንደር አሰሳ ጀምረዋል፡፡ መስተንግዶዋ አስጊ ሁኔታ ውስጥ የገባው ብራዚል ቡድኗ የ1950ውን ታሪክ እንዳይደግም ብትመኝም ከወዲሁ የተሰማው የአሰልጣኝ ሶኮላሬ የታክስ ጉዳይ የቡድኑን ትኩረት እንዳይከፋፍለው ስጋት ፈጥሮአል፡፡ ሆኖም ስኮላሬ ምንም አይነት የታክስ ማጭበርበር አለመፈፀማቸውን እየተናገሩ ነው፣ እርሳቸው ይህን ቢሉም የብራዚል መንግስት ግን የ7 ሚሊየን ታክስ ምርመራውን መጀመሩን የፖርቹጋል ጋዜጣ ዘግቦአል፣ ስኮላሬ ግን በሰራሁበት ሀገር ሁሉ ታክሴን በሚገባ ከፍያለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የታክሱ ጉዳይ የተነሳው ስኮላሬ ከ2003 እስከ 2008 የፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በሆኑበት ወቅት ነው፣ የ65 አመቱ የቀድሞ የቼልሲ አሰልጣኝ 23 አባላት ያሉትን ቡድናቸውን በዚህ ሳምንት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፣ በ2002 ከብራዚል ጋር ዋንጫውን ያነሱት ስኮላሬ በቡድናቸው ልምድ ያላቸውን ካካን ሮቢኒሆን ሮናልዲኖሆን አላካተቱም በምትኩ ቡድኑን በወጣት ገምብተውታል ፡፡ ተጨማሪ...diretu.be/579364
Posted on: Wed, 14 May 2014 17:30:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015