Somali teen who flew inside airplane wheel-well to see his mother - TopicsExpress



          

Somali teen who flew inside airplane wheel-well to see his mother in Ethiopia ... see at... diretu.be/332983 | እናቱን ፍለጋ የቦይንግ 767 ጎማ ውስጥ ተደብቆ በ5 ሰዓታት በረራ ከካሊፎርኒያ ሐዋይ የገባው የ15 ዓመቱ ሶማሊያዊ ወጣት ጉዳይ ዓለምን አስደንቋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ያለችው የ15 ዓመቱ ሶማሊያዊ ታዳጊ ያህያ አብዲ እናት “አሜሪካ መጥቼ ልጄን አገኘዋለሁ…እስከዛው የአሜሪካ መንግስት ልጄን ይንከባከብልኝ” ማለቷ ተዘግቧል፡፡ ጉዳዩ እንዲህ ነው… የወጣቱ ያህያ አብዲ አባት ከዓመታት በፊት ነበር ከያህያ እናት ጋር ተለያይቶ ሌላ ሴት አግብቶ ወደ አሜሪካ ያቀናው፡፡ እናም የያህያ አባት ለያህያ፣ ያስርና ናጅማ ለተባሉት ልጆቹ እናታችሁ ሞቃዲሾ ውስጥ በሮኬት ጥቃት ተገድላለች ብሎ ነግሯቸዋል፡፡ የእናቱን በሕይወት መኖር የዛሬ ሁለት ዓመት በካሊፎርኒያ ከሚኖሩ የሶማሌ ማሕበረሰብ አባላት የተረዳው ወጣቱ ያህያ ታዲያ…የእናቱ ነገር ሲያብሰለስለው ቆይቶ ባለፈው እሁድ ከካሊፎርኒያ ሐዋይ የሚበር ቦይንግ 767 ጎማ ውስጥ ተደብቆ ለ5 ሰዓታት በመብረር ሐዋይ በሰላም ሲደርስ ዓለም ጉድ ነው ያለው፡፡ የሜይል ኦን ላይኑ ዘጋቢ በአስተርጓሚ ያናገራትና ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ የመጠለያ ካምፕ ውስጥ ያለችው የያህያ እናት…“ልጄ አደገኛ ጉዞ ማድረጉን ሰምቻለሁ…የልጆቼ ነገር ሁሌ እንቅልፍ እንደነሳኝ፣ እንዳለቀስኩ ነው፡፡ አሜሪካ ለመግባት በሒደት ላይ ስላለሁ ለልጄ ያህያ እናትህ በሕይወት አለሁ…መጥቼ አንተንና ሁለቱን ልጆቼን አገኛለሁ፡፡ እስከዛው ግን ታግሰህ ጠብቀኝ” የሚል መልዕክቷን አስተላልፋለች፡፡
Posted on: Mon, 28 Apr 2014 11:56:07 +0000

Trending Topics



/div>

Recently Viewed Topics




© 2015