ለንሰሃ የሚጠቅመን ራስን መመርመርያ - TopicsExpress



          

ለንሰሃ የሚጠቅመን ራስን መመርመርያ ጥያቄዎች 1. የሌሎችን ምስጋና ለመስማት መናፈቅ 2. ሰው ማማት እና ሃሜቱን እውነት ወይም ሃሰት መሆኑን ሳታረጋግጥ/ጪ ማሰራጨት 3. የድሃዎችን ድምጽ ሰምቶ ማለፍ 4. ለንሰሃ የሚጠራን የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ሰምቶ ዝም ማለት 5. መሳደብ መዋሸት እና መማል 6. መኮነን ማሾፍ ከንቱ ክርክር 7. ሃይማኖትህን አለመናገር: እግዚያብሄር ላይ ማጉረምረም ወይም መሳደብ 8. የሌሎችን ስኬት ሲያዩ ቅር መሰኘት ወይም ውድቀታቸው ላይ የደስታ ስሜት መሰማት 9. ምስጋና ለማግኘት ስለራስ ጽድቅ ማውራት: ምክር አለመቀበል 10. በቅዳሴ ግዜ መሳቅ ማውራት 11. የሌሎችን ሃብት ጌጥ...መመኘት 12. ለሞራል የማይገቡ ነገሮችን መመልከት 13. ስለፍትወት ማሰብ: በሀጥያት ሰለመውደቅ ማሰብ 14. እውነታ ያልሆኑ ቅዥት ነገሮችን ማሰብ 15. ከልብ ያልሆነ ምስጋና ማመስገን 16. ተግባር የሌለበት እምነት: ለምሳሌ ቄሱ "በንሰሃ ያላችሁ ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ" ሲባል ንሰሃ ሳትገባ ታደርጋለህ? 17. ኩራት አለብህ: ሰዎች ስላላመሰገኑህ ትርቃቸዋለህ ወይስ ምኞት አለብህ 18. ዝሙት ፈጽመሃል? ሰርቀሃል? ከሚስትህ/ባልሽ የደበቅሀው/ሽው እውነት አለ? 19. ከቢሮ ሰርቀሃል? ለምሳሌ ስልክ ለራስህ ጉዳይ ተጠቅመሃል ወይም እስኪብርቶ ወስደሃል? ወይም ተውሰህ ሳትመልስ የሰረቅሃቸው ነገሮች አሉ? 20. ስትሸጥ ሰዎችን አታለሃል? ጉቦ ሰተሃል/ተቀብለሃል 21. የስራ ግዜህን በአግባቡ ተጠቅመሃል? ስራህን በቸልተኝነት ሰርተሃል? 22. ስልጣንህን ተጠቅመህ ሰው በድለሃል? የሃሰት ምስክር ሆነሃል? ቁማር ተጫውተሃል 23.የሌሎችን ምስጢር ሰርቀሃል? በፈተና ግዜ አታለሃል? 24. የአልኮል ወይም መጠጥ ሱስ አለብህ? ዳንስ በሰርግ ላይ ደንሰሃል? 25. አለመታዘዝ እና ማማረር ይታይብሀል? 26. ድሃዎችን ወይም የእግዚያብሄር ሰዎች አታለሃል? አቃለሃል? 27. ጥሩን በበጎ መልሰህ ታውቃለህ? ወንድሞችህ ላይ የመራራት ስሜት በቀላሉ አታሳይም? 28. በፍጹም ልብህ ጸሎት ታደርጋለህ? ቀንህን በጸሎት ትጀምራለህ? ቅዳሴ አርፍደህ ትመጣለህ? 29. አጽዋማትን ትጾማለህ? መጽሃፍ ቅዱስ ታነባለህ? ከምትትገብረው በላይ ታነባለህ? 30. በስራህ ታማኝ ነህ? ሁሉን ትወዳለህ? አስራት ትከፍላለህ? የታመሙ ትጠይቃለህ? የታሰረ ታስፈታለህ? ዘወትር ንሰሃ ትገባለህ? .......... ንሰሃ እንግባ! በዚህም ግዜ እያንዳንዱን ሃጥያት አስታውስ ተናገር:: ምክኒያት አንደርድር:: ዘወትር ንሰሃ እንግባ!
Posted on: Sat, 17 Aug 2013 18:26:04 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015