ሐሰን ታጁ ከፋክት መፅሄት ጋር ካደረገው - TopicsExpress



          

ሐሰን ታጁ ከፋክት መፅሄት ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ፡፡በቅድሚያ ስል ቃለምልልሱ አንዲት መረጃ ላካፍላችሁBY:MUSLIM WEDAJEየኢትዬጲያ ሙስሊሞችን ሰላማዊ ትግል በማስመልከት ፋክት መፅሄት የሃሰን ታጁን ራዕይ እና የህዝበ ሙስሊሙን አቋም በአንድ መፅሄት ላይ ለማውጣት እቅድ ነድፈው የነበረ ቢሆንም መንግስታዊ ራዕይን የሰነቀውን ሃሳብ ከህዝበ ሙስሊሙ አቋም ጋር አብሮ መቅረቡ ህዝበ ሙስሊሙን መናቅ ይሆናል በሚል እሳቤ በዚህ እትሙ ላይ መንግሰታዊ ራዕይን ያነገበውን ሃሳብ ብቻውን ይታተም ዘንድ ታምኖበት ለብቻው እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡የህዝበ ሙስሊሙን አቋም በማሰመልከት የተለያዩ ሙስሊሞችን ኢንተርቪው ላይፍ መፅሄት አድርጋ የነበረ ሲሆን ከዚህ ሃሳብ ጋር አብሮ መውጣት ስለሌለበት በሚል ሳይወጣ መቅረቱን ታውቁት ዘንድ እቺን መረጃ ቢጤ ጣል አደረኩላችሁ፡፤ከፋክት መፅሄት “ኢትዬጲያ ካፈራቻቸው የእስልምና ልሂቅ አንዱ ከሆኑት ኡስታዝ ሐሰን ታጁ” ቃለመጠይቅ የተወሰደበቅንፍ የተቀመጡት የግሌ ማብራሪያዎቸ ናቸው• የሙስሊሙ ተቃውሞ እየተመራ ያለው በስውር በመሆኑ ከአልቃኢዳጋር ያመሳስለዋል፡፤ አልቃኢዳ በስውር በመመራቱ በደህንነቲቶች መጫወቻ ሆኗል፡፤ የሙስሊሙ ትግልም ተመሳሳይ አደጋ ሊደርስብት ስለሚችል ያሰጋል፡፤የሆነ አካል ሊጠልፈው እና ወዳልተፈለገ መንገድ ውስጥ ሊከተው ይችላል፡፡መንግስት ይጠልፈዋል ማለቴ ግን አይደለም• አብዛኛው ሰው ጥቅም እና ጉዳቱን ሳያመዛዝን ነው የሚነዳው• ከኮሚቴው ጎን የተገነጠልነው ከኮሚቴው ጋር የአፈፃፀም ልዩነት ስለነበረን ነው• የሙስሊሙ ጥያቄ በመርህ ደረጃ መመለሱን የታሰሩትም ሙስሊሞች በአንደበታቸው ተናግረዋል• መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አልገባም ነገር ግን በሙስሊሙ አና በመንግስት መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ነው፡ በመካከላቸው የነበረው ድልድል ተሰብሮ ነው፡፡• ግጭቱ እንደሚፈራው አደጋ አላስከተለም፡፡ ይህም ምንም ይሁን ምን የመንግስትን ትግስት ታያለህ(በኢድ በአል ቀን እርጉዝ ሴት ተደብድባ መገደሏ የመንግስትን ታጋሽነት በይበልጥ ያሳየ ነው)• ኮሚቴዎቹ የስነ ስርአት እና የአፈፃፀም ጉድለት አለባቸው በማለት በሚዲያ ኮሚቴው ሲታሰር ዶ/ር ኢድሪስ መግለጫ ሰቷል• ሶስት መፍትሄዎችን አቅርቤ ነበር፡፤ደም የሚያፋስሱ መንገዶችን አቁሙ፡፤ የህዝቡን ሙቀት ጠብቁ፡፡ ያለውን የህዝብ ጉልበት ወደ ልማት ወደ ትምህርት አስፋፉት የሚል(ሰላማዊ የመብት ማስከበር ሂደትን ወደ ልማት እናዙረው ማለቱ ነው)• ኮሚቴው ሁለት አማራጭ ብቻ ነው ያለው፡፤ ወይ በነፃ መለቀቅ ወይም ይቅርታ መጠየቅ፡፡እኔ ይቅርታ መጠየቃቸውን ነው እንደፖለቲካ ተገቢ ነው ብዬ የማምነው• የታሰሩት ልጆች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በፊት 4 ወራት ነበር፡፡ በዛ ወቅት የማግባባበት መስመሩ ቢኖር መጠቀም ይቻል ነበር(እነዛን ከሱ ቢበልጡት እንጂ የማያንሱትን ታላላቅ ኡስታዞቻችንን፣አሊሞችን ነው ልጆች አያለ በንቀት የሚጠራቸው)• ትግሉ በስሜት ብቻ ነው የሚመራው• ዲያስፖራው ዋና አላማው መንግስትን መገልበጥ ነው(የዲስፖራው ሙስሊሞች አላማችሁ መንግስት መገልበጥ ነው ለካ!!!!)• በዲያስፖራ ያለው የሌላ እምነት ተከታዬች አላሁ አክር እያሉ ሙስሊሙን መደገፋቸው ለሙስሊሙ አስበው ሳይሆን ለራሳቸው ፖለቲካዊ አጀንዳ ነው(በውጪ የሚኖሩ ክርስቲያን እና ሙስሊሞች በጋራ በመሆን ሃይማኖታዊ የሙስሊሞች ሃይማኖታዊ መብት ይከበር ማለታቸው የፖለቲካ አጀንዳ ነው ተባለ)• ትግሉ ውስጥ መንግስትን ለመገልበጥ ያሰበ ፖለቲካዊ አጀንዳ ገብቷበታል፡፤ በተለየ ዲያስፖራው ላይ• ኢህአዴግ ቢወድቅ ባይወድቅ ጉዳዬ አይደለም፡፡ 6ሚሊዬን አባላት አሉት፡፡ እነሱ ይጨነቁለት• የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደህዝብ መጠራጠር ሳይሆን ማመን ነው ያለብን፡፡ ወደፊት ለማስተካከል መሞከር አለብን፡:የተቀረውን ደግሞ መፅሄቱን ገዝታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ፡፡ ደስ ባይላችሁም እስልምና ሰው እንዲደሰትብህ ብለህ መሰራት እንደሌለብህ ስለሚያስተምር ችግር የለውም፡፤ ረጋ ብላችሁ አንብቡት ትደሰቱበታላችሁ
Posted on: Sun, 08 Sep 2013 06:14:11 +0000

Trending Topics



31971773">Gotta love the English Language 1) The bandage was wound around
This year, Pope Francis led his first procession through Rome. A
The Man Of the Hour- Anderson Cooper He may have left the
Reflecting back, I believe it was May 12th 1984 when I first laid

Recently Viewed Topics




© 2015