ሰላም ጤና ይስጥልኝ ሃና እባላለው - TopicsExpress



          

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ሃና እባላለው ከዱባይ ከመጣሁ 2አመት አልፎኛል በኮንትራት የመጣሁበት ቤት ገና ወርም ሳይሞላኝ አሰሪዬ በተደጋጋሚ አስገድዶ ይደፍረኝ ነበር ገናም ልጅ ስለነበርኩ መቇቇም አቃተኝ እናም ወደመክተብ መልስኝ እያልኩ ቀን ከሌሊት አለቅስ ስለነበር ወደ መክተብ መለሱኝ:: መክተብ ውስጥ ሰውን ከማስተናገድ አቅም በላይ የተጨናነቀው ነው በዛም ላይ በጣም ርሃብ አለ::ህንድ ኤንዶንዢያ ፊሊፒንስ ሴሪላንካ እናም እኛ ኢትዮጵያኖች በአንድ ክፍል ውስጥ ታጉረን አሰሪ ከዛሬ ነገ በማለት እንጠብቃለን እንደ እድል ነው አሰሬዎቹ አይተው መርጠው ነው የሚወስዱት እኔም አሰሬ በመጠባበቅ ቀናቶችን አስቆጠርኩ ግን ማንም ሊወስደኝ የሚመጣ ስፖንሰር አጣሁ እዚሁ ካለችው አንድ ኢትዮጵያዊ ጋር ተመካከርን ከመክተብ ውስጥ ለመጥፋት መክተብ ውስጥ ካሜራ አለ በዛ ላይ ማታ ሲወጡ ከውጭ ተቆልፍብን ነው በቃ በሆነ መንገድ ከዚህ መክተብ ማምለጥ አለብን ተባብለን ተማከርን ሁኔታዎች ሲመቻችልን በመስኮት ለማምለጥ ስንዘጋጅ የሆነች ፌሊፒኒ ልትይዘን ሙከራ ስታደረግ ደበደበናትና በመስኮት ዘለን አመለጥን :: እናም ጠፍቼ በመስራት ላይ እገኛለው አሁን ግን ወደ አገሬ መግባት ስላሰብኩ በጣም ፈራሁ ወንጀል የሌለባቸው ሰዎች መሳፈር ሲፈልጉ እጃቸውን ለፖሊስ ይሰጣሉ እኔ ግን ያኔ የደበደብኳት ፊሊፒኒ ስላለች ወንጀሉ ይከብድብኛል ውድ የዚህ ጹሁፍ አንባቢ በሙሉ እባካችሁን እጄን ለፖሊስ ሳልሰጥ በሌላ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የምገባበት መንገድ ካለ ተባበሩኝ ሃና ከዱባይ
Posted on: Mon, 02 Sep 2013 20:58:10 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015