ሰሞኑን ስላያኋቸው ሁለት ወሳኝ ወሳኝ - TopicsExpress



          

ሰሞኑን ስላያኋቸው ሁለት ወሳኝ ወሳኝ ቃለ ምልልሶች አንድ ጨዋታ ይዤ ልከሰት አስቤ ትላንት ጀምሬው ነበር አላልቅህ አለኝ… "ወጋሚ" በሉት… ምናገባን ደስ ባለው ጊዜ ይለቅ ባለቀ ጊዜ ማቅረብ ነው የእኛ ስራ… እስከዛ ግን፤ ይቺን እንካችሁማ… አንድ በዕድሜ ገፋ ያሉ ሴትዮ በግ ይዘው ገበያ ይወጣሉ፡፡ ታድያ ወደ አራት የሚጠጉ የተረገሙ ሌቦች በሆነ ዘዴ በጉን ሊነጥቋቸው ፈለጉ በጉልበት ቢነጠቋቸው አካባቢው "ኡኡ" ብሎ እንደሚያስጥላቸው ተረዱ እናም አንድ መላ መቱ… ተሰበጣጥረው ቆሙ ከዛ አንዱ ሌባ በዕድሜ የገፉት ባለ በግ ሴትዮ አጠገቡ ሲደርሱ… "እማማ ይቺን ውሻ ጠንቀቅ እያሉ ሰው ከነከሰች ጉድ ይሆናሉ" አላቸው፡፡ ሴትዮዋ የሌባው እርግጠኝነት አጠራጥሯቸው "አ…ረግ ምን ነክቶሃን… ይሄ በግ እኮ ነው… የምን ውሻ አመጣህብኝ" ሲሉ መለሱ… ዝም አላቸው እና አለፋቸው፡፡ ትንሽ እንደሄዱ ደግሞ ሌላኛው ሌባ "እንዴ ምን ነካዎት እናቴ ውሻዎት ነክሶኝ ነበርኮ ገበያ መሃል ውሻ ይዞ መዞር ምን ይሉት ፈሊጥ ነው… " አላቸው፡፡ ሴትየዋ ግራ ተጋቡ ዛሬ ሰዉ ሁሉ አብዷል እንዴ ብለው ትተውት ሄድ አሉ፡፡ ድጋሚ ሶስተኛ ሰው… "እማማ ውሻዎ ያምራል ግን ገበያ መሃል ጥሩ አይደለም ሰው እንዳይተናኮልብዎ… " አላቸውና አለፋቸው… ይሄኔ ሴትየዋ… እውነትም ይሄ ነገር በግ ሳሆን ውሻ ነው ማለት ነው… ብለው ተጠራጠሩ… በጉን የያዙበትን ገመድ ሊለቁት ዳዳቸው፡፡ እጃቸውን እንዳላሉ ትንስ ራመድ ሲሉ አራተኛው ሰው "እማማ በፈጣሪ ይዤዎታለሁ…. እኔ ውሻ እፈራለሁ ዘወር ያድርጉልኝ… " ብሎ ሲወተውታቸው አመኑ፡፡ ጭራሽ ራሳቸውን መውቀስ ጀመሩ…. ምነ ነከቶኝ ውሻ ይዤ ገበያ መሃል መጣሁ ደግሞስ ከየት አመጣሁት…. ብለው ለቀቁት እና ራሳቸውም ሸሽተው ከገበያው አካባቢ ተሰወሩ፡፡ የመጀመሪያው ሌባ ታድያ ገመዱን ቀብ አደረገው… ከዛም "እቤት ተቀልቦ ያደገ የሞከተ በግ ነው" ብሎ በደህና ዋጋ ሸጠው፡፡ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል፡፡ ግን እውነት አይሆንም፡፡ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተደጋጋሚ ባንዲራ ሲያቃጥሉ እየተባለ የተነገረላቸው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬ ራሳቸው ባንዲራ ሆነው አደባባይ ወጥተዋል፡፡ ሲያቃጥሉ፣ ሲያቃጥሉ፣ ሲያቃጥሉ የሚለው ተደጋግሞ ሲነገር እውነት የመሰላችሁ ወዳጆች ነገሩ እውነት ይመስላል አንጂ እውነት አይደለም፡፡ ይህንን ለማረጋገጥ ዛሬ አደባባይ የወጡትን ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ማየት በቂ ነው፡፡ መንግስቴ ግን መቼ ይሆን ከአራቱ ሌቦች የተሸለ አስተዳደር የሚያመጣልን ብዬ ሳስብ ይደክመኛል!
Posted on: Thu, 08 Aug 2013 07:34:02 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015