በእውነቱ ወንድማችን በጣም ከራሱ ጋር - TopicsExpress



          

በእውነቱ ወንድማችን በጣም ከራሱ ጋር የታረቀ ኢትዮጵያዊ ነው። እንደዚህ አይነት ሀሳብ የሚጋሩ ሰዎች ብዙ ናቸው ነገር ግን ወደ መድረክ ብሎም ወደ ሚዲያዎች እየመጡ ሀሳባቸውን ለማጋራት እንካሰላንትያውን አይፈልጉትም ሊያስተናግዱዋቸው ፈቃደኛ የሚሆኑትም ውስን ናቸው። ሀሳቡ እውነትም መልካምም ነው። አገራችን አዲስ ሀሳብና አዲስ ራዕይ ያስፈልጋታል። መቻቻል፤መደማመጥና ለህግ የበላይነት ተገዢ መሆን ዋነኛ መርሆ መሆን አለባቸው። በምሁራን የተጣበበችው ሰሜን አሜሪካ ኮሞፓስ እንዳጣች መርከብ ስትዋዥቅ አራት አስርተ አመታት አለፉ። በኢትዮጵያውያን መካከል የሀሳብ ልዩነት የማይከበርባት ልቅ የአሜሪካ ዋና መዲና ሙያውን ሊያበረክት የሚችለውን የሰለጠነ ባለሙያ በሙሉ ከስራ ወደ ሰበርብ መኖሪያው እንዲከተት አድርጋለች። አልፋ ተርፋም ይህን እንጀራ ብላ፤በዛ አውሮፕላን ሂድ አትሂድ እያሉ ትዛዝ የሚሰጡ ፊትአውራሪዎች የሞሉባት። ይገርማል አለ ጋሽ ጥላሁን ነፍሱን ይማረውና፣
Posted on: Wed, 13 Aug 2014 02:23:45 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015