ቢስሚላሂራህማኒራሂም BY Malcolm king - TopicsExpress



          

ቢስሚላሂራህማኒራሂም BY Malcolm king (M.K.) በዛሬው እለት በጣም ስለገረሙኝ ነገሮች ትንሽ ማለት ፈለኩኝ ከጥቂት ደቂቃ በፊት ስለ ዶዶላ ፖስት የተደረገ ነገር ኣይቼ መንግስት ሙስሊሙን ለመከፋፈል የጠራው ስብሰባ እንደከሸፈ ሳነብ ምንም ዜናው የሚያስደስት ቢሆንም እኔን ግን ያሳሰበኝ የሙስሊሙ የዋህነት ነው በተደጋጋሚ የወያኔ መርዘኛነት የሚጋባህ ሲነድፍህ ነው እያልን ስናወራ እንዳልቆየን ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው መንግስት ስብሰባ እያለ ጠንካራ ሙስሊሞችን ማደኛ ስብሰባ ሲጠራ እየተጓተትን የምንሄደው? በዛሬው ስብሰባ የሚሰማቹህን የተናገራቹህ ሰዎች እራሳቹህን ጠብቁ ሌሎቻችን የምንሰማውን ነገር እንደ ሙዚቃ ሳንቆጥር ወያኔ በሚጠራቸው ስብሰባወች ላይ እንዳንገኝ ምንም ሌላ አማራጭ ኣጥተን እንኩዋን ብንሄድ ኣስተያየት ከመስጠት እንቆጠብ ሌላው ሰሞኑን መንግስት ሁለት መስጊዶችን ለገርባ ሙስሊሞች እንደመለሰና ህዝቡም ደስተኛ እንደሆነ ኣንብቤ ነበር በቅድሚያ መስጊዶች በኣጠቃላይ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ንብረቶች ናቸው ሁለተኛ በምንም ኣይነት ከወያኔ ምንም ጥሩ ነገር ስለማይመጣ ምናልባት ሃገር ለቀው የሄዱትን ሰዎች ሰላም የሰፈነ ኣስመስሎ ሲመለሱ ለመያዝ ስለሆነ ህዝቡ ኣሁንም ኣስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ላሳስብ እወዳለሁ በመጨረሻ ሳስበው ሁሉ የሚያመኝ የሙስሊሙ በህገወጡ መጅሊስ በኩል ፕሮሰስ ወደ ሃጅ ለመሄድ መጀመሩ ነው ሰሞኑን ኢሄንን በተመለከተ ከጻፍኩኝ ጀምሮ ሰዎች በመሴጅ ስለ ብዙ ነገር እያጫወቱኝ ሲሆን የኣንዳንዶቹ ወላጆች ፓስፖርት ሊያወጡ ሄደው ለሶስት ወር እንደተቀጠሩና የፈለጉትም ለሃጅ ስለሆነ ቀኑ ማለፉን ሲገልጹ ፓስፖርቱን ለማግኘት ገንዘብ ሃምሳ ሺ ብር ለመጅሊስ የሚከፈል ተቀማጭ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን ገልጸዋል በቅድሚያ ፓስፖርት እጃቹህ ላይ የሚገኝ ሰዎች በጉዞ ወኪሎች የህገወጡን መጅሊስ ግማሽ ዋጋ ብቻ በመጠየቅ ሃጅ እንደሚያስደርጉ ሰምቻለሁ ሌሎቻችን ግን ፓስፖርት የሌለን ወላሂ እንደኔ እንደኔ ኣላህ ኒያቹህን ነው የሚያየው ለእነዚያ ኣዛውንቶች ሴቶች ነፍሰ ጡሮች እንዲደበደቡ እንዲገደሉ መንግስትን እርምጃ እንዲወስድ ለሚማጸኑ ኣረመኔዎች( 175,000,000) ኣንድ መቶ ሰባ ኣምስት ሚሊዮን ብር በዚህ ሃጅ ብቻ ገቢ ኣግኝተው ኪሳቸውን እንዲያደልቡ ማድረግ ሸሂድ በሆኑት በታሰሩት በተደበደቡት ሙስሊም ወንድኖችና እህቶች ላይ መቀለድ ይመስለኛል እባካቹህ ጥንካሬ ኣንድነት ቆራጥነት ከሌለን መንግስት ላይ ጫና ማሳደርም ሆነ ትግሉን በድል ለመወጣት ኣስቸጋሪ ነው የሚሆነው የ ኣላህ ኡማውን ከሚጎዱ ነገሮች የምእራብና የምስራቅ ያህል ኣርቀን ኣሜን
Posted on: Mon, 12 Aug 2013 18:54:04 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015