ተፈኩር በ አፍራህ ቢንት ዘከሪያ እስቲ - TopicsExpress



          

ተፈኩር በ አፍራህ ቢንት ዘከሪያ እስቲ ለአፍታ ቆም ብለን እናሰብ፤ እራሳችንን በተፈኩር አለም እንመስጥ፤ አይናችንን ወደ ሰማይ ሰክተን ይህን ግዙፍ ምትሃታዊ ዩኒቨረስ እንመልከት! ፀሀይ! ከምድራችን በ150 ሚሊዮን ኪሎ ሜትሮች ትርቃለች፡፡ ምንም እንኳን መካከለኛ መጠን ካላቸው ኮከቦች ብትመደብም የምድራችንን ያህል የግዝፈት መጠን ካላቸው 1,300,000 ፕላኔቶች ድምር እኩል ትሰፋለች፡፡ የውጭ አካሏ የሙቀት መጠን 6,000 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሲሆን በውስጧ ያመቀችው ሙቀት እስከ 20,000,000 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ይደርሳል፡፡ አጂብ! 100 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ውሃን ለማንተክተክ በቂ እንደሆነ እናስታውስ፡፡ በዛቢያዋ የምታደርገው የሽክርክሪት ጉዞ 720,000 ኪሎ ሜትሮች በሰአት ሲሆን በአንድ ቀን ሲሰላ 17,000,280 ኪሎ ሜትሮችን ትጓዛለች ማለት ነው፡፡ በፀሀይ ውስጥ በእያንዳንዷ ሰከንድ 564,000,000 ቶን ሀይድሮጅን ወደ 56,000,000 ቶን ሂልየም ይለወጣል፡፡ የ4 ሚሊዮን ቶኑ ልዩነት በተለያዩ ኃይላት ከአካሏ ወደ ውጪ የሚተፋ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ሲቀመጥ ፀሀይ በእያንዳንዱ ሰከንድ 4 ሚሊዮን ቶን፤ በደቂቃ 240 ሚሊዮን ቶን ንጥረ ነገሮችን ታጣለች፡፡እንግዲህ ፀሀይ በዚህ መልኩ ለ3 ቢሊየን አመታት ኃይል ካወጣችና ካጣች እስካሁን ያጣችው ንጥረ ነገር 378,432,000,000,000,000,000,000 ቶን ይሆናል ማለት ነው፡፡ገብቷችኋል አይደል ያጀመዓ 1 ቶን ማለት 1000 ኪሎ ነው! ይህ ግን ፀሀይ ካላት አጠቃላይ ክብደት 1/5,000ኛ ብቻ ነው፡፡ ምድራችን ከዚህች ድንቅ ኮከብ በሙቀቷም እንዳንቀልጥ ከጥቅሟም እንዳናጣ በprecise perfection በተመጠነና በጥናቃቄ በተሰላ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ፀሀይ ኃይሏንና ውበቷን ሳታጣ በምድር ላይ ላሉ ፍጥረታት ለሚሊዮን አመታት ጨረሯን ስትልክ ኖራለች፡፡ እስካሁን ጥቂት ያልንላት ፀሀይ በሚልኪዌይ ጋላክሲያችን ውስጥ ካሉት 200,000 ከዋክብት መካከል አንዷ ነች፡፡ ይህ ሚልኪዌይ ጋላክሲ ደግሞ ዩኒቨርስ ውስጥ ካሉት በመቶ ቢሊዮን ከሚቆጠሩ ጋላክሲዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ብርሃን በአንድ ሰከንድ 300,000 ኪሎ ሜትሮችን ይጓዛል፡፡ በዚህ ፍጥነት ከአንዱ ጋላክሲ ወደ ሌላው ለመሄድ 100,000 የብርሃን አመታትን ይፈጃል፡፡ አንድ ሰው (superman እንበለው) ከምድራችን ተነስቶ ወደ ሚልኪዌይ ጋላክሲ እምብርት በብርሀን ፍጥነት እየበረረ ለመጓዝ ትሪሊዮን ኪሎ ሜትሮችን ማቋረጥ አለበት፡፡ ለፈጠረን ጌታ ላቅ ያለ ጥራትና ምስጋና ይገባው! እንግዲህ ከ ‘አላሁ አክበር’ ውጪ ምን ምለው አለኝ?! ሱብሃነ ረቢየል ዓዚም ያረበል ዓለሚን! አላሁአክበር!!! ምንጭ፡- ኢስላም ብቸኛው መለኮታዊ ሐይማኖት፤ በዶ/ር ሙራድ ኪያት
Posted on: Thu, 22 Aug 2013 12:53:51 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015