አቦሸማኔን የረቱ አፍሪካዊ - TopicsExpress



          

አቦሸማኔን የረቱ አፍሪካዊ እግሮች --------------------------- እስከዛሬ የምድራችን ፈጣኑ እንሰሳ አቦሸማኔ ነበር፡፡ አሁን ግን የአቦሸማኔ ዘር ይሄን ሬከርድ በኬንያው ገበሬ ኑር ኦስማን እና ሶሰት ጓደኞቹ ተነጥቋል፡፡ ገበሬው ኑር ከየዱሩ ብቅ እያሉ ፍየሎቹን ዋጥ ስልቅጥ በሚያደርጉ አቦሸማኔዎች ሲማረር ኖሯል፡፡ ታዲያ ሰሞኑን ሁለት አገር ሰላም ያሉ አቦሸማኔዎች የልማዳቸውን ለማድረስ ወደ ኑር ሰፈር ብቅ ብለው የእለት ፍየላቸውን ያማርጣሉ፡፡ ኑር ደረሰባቸው፡፡ በተለምዶ እንደሚደረገው ግን ጠመንጃውን አላቀባበለባቸውም፡፡ ጎረቤት ያሉ ሶስት ባልንጀሮቹን አስተባብሮ በጠራራ ፀሃይ ከ6 ኪሎ ሜትር በላይ ሁለቱን አቦሸማኔዎች በሩጫ ማሳደድ ያዘ፡፡ በእርሱና በጓደኞቹ ፈጣን እግሮች የተረቱትን ሁለቱንም አቦሸማኔዎቸ ጥፍንግ አድርጎ ይዞ ለኬንያ የዱር እንሰሳት ቢሮ ‹‹እንኩ›› ብሎ አስረክቧል፡፡ ‹‹ኑር፤ ምነው ይሄን ያህል ልፋት?››ላሉት ደግሞ ‹‹የሮጥነው ለስፖርት አይደለም፡፡ እነዚህ አቦሸማኔዎች ፍየሎቼን በሙሉ ፈጅተውብኛል፡፡ ካሳዬን እፈልጋለሁ›› ብሏል፡፡ እንደ አፍሪካዊ ሆኜ ሳስበው፤ በነ ኑር ታሪክ ውስጥ የአፍሪካ አትሌቶች አበረታች እፅ ምን እንደሆነ ቅልብጭ ብሎ ታይቶኛል፡፡ ድህነት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊ ብቻ ሆኜ ሳስበው ደግሞ ነገሩ እምብዛም አላማረኝም፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዲሬሽን ሰምቶ ይሆን እንዴ?
Posted on: Sun, 24 Nov 2013 08:02:56 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015