አቶ ኃይለማርያም ለምን ጨፈሩ • Hailemariam - TopicsExpress



          

አቶ ኃይለማርያም ለምን ጨፈሩ • Hailemariam Desalegn Prime Minister of Ethiopia • Hailemariam Desalegn Boshe is an Ethiopian politician. He is the Prime Minister of Ethiopia. Hailemariam Desalegn previously served as Deputy Prime Minister and Minister of Foreign Affairs under Prime Minister Meles Zenawi from 2010 to 2012. Wikipedia • Born: July 19, 1965 (age 48), Boloso Sore • Spouse: Roman Tesfaye (m. 1989) • Office: Prime Minister of Ethiopia since 2012 • Education: Azusa Pacific University, Arba Minch University, Tampere University of Technology, Addis Ababa University • Children: Johanna Hailemariam በጣም የገረመኝ ነገር አንዳንድ ጦማረኞች በእርሳቸው መጨፈር ተገርመው ክሮፕ የተደረገውን የተወሰነ የተስተካከለውን Edited Picture/ ፎቶ ፖስት በማድረግ ስለ እርሳቸው ፖለቲከኛነት ሳይሆን ጭፈራቸውን ሊያብራሩልን ይፈልጋሉ፡፡መጨፈር ብርቅ ነው እንዴ ወይስ ለፈጣሪ አግዘው ነው? .. ምናልባት በአጨፋፈራቸው ስታይል ፈጣሪ ከተቀየማቸው/ጭፈራ ከእርሳቸው አይጠበቅም ምክንያቱም ሃይማኖተኛ ነኝ ስለሚሉ?/ማን ያውቃል እርሳቸው ከፈጣሪያቸው ጋር ሠላም ፈጥረው ይሆናል… ይቅርታ ጠይቀውት/፡፡ ምናልባት የሌሎች ባለ ስልጣናት ጭፈራና መዝፈን ምንም ሳይባል ለምን የእርሳቸው መጨፈርን ለማጉላት ተፈለገ?.. ወይስ የእርሳቸው መጨፈር አገለግለዋለው ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ይነካዋል..? ወይስ ከጭፈራው በስተ ጀርባ ምን አይነት ነገር ሊኖር ይችላል ተብሎ ታስቧል..? ወይስ የጭፈራው አይነት ፖለቲካዊ እንድምታ አለው…? ወይስ በሚከተለት ቤተ እምነት ዘንድ መጨፈር ክልክል ስለሆነ እርሳቸውን ለማስጠቆር ነው…? እኔ እስከ ማውቀው ሃገራችን ውስጥ ያሉ አብዛኛው የእምነት ተቋማት/ክርስቲያኑም ሙስሊሙም ሳይለይ…./ ዘፈንንና ጭፈራን ፈጣሪ እንደማይፈቅደው ነው ሲናገሩ የምሰማው… አንዳንዱ ዘፋኝ እምነቴ ባይፈቅድልኝም… ሲል በተለያዩ ቃለ መጠይቆች እንሰማለን…. ታዲያ የእርሳቸው መጨፈር ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ለምን ማነጋገር ጀመረ…? የሥራ ባልደረባቸው የውጪ ጉዳይ ሚንስትራችንም ጥሩ ጊታሪስት እንደሆኑ መድረክ ላይ አሳይተውናል • Tedros Adhanom Ghebreyesus is an Ethiopian academic and politician who currently serves as the Minister of Foreign Affairs. Formerly, he was Minister of Health from 2005 to 2012. Wikipedia • Born: Asmara, Eritrea • Nationality: Ethiopian • Party: Ethiopian Peoples Revolutionary Democratic Front • Education: University of Nottingham,University of London, University of Asmara …. እና ታዲያ ሰው ለሙዚቃ ያለውን ስሜት መግለፅ አይችልም እንዴ ከፈለገ…? ወይስ ሙዚቃ ከሃገራችን ፖለቲካ አስተሳሰብ ጋር የሚገናኝ ነው…? ወይስ ይህንን ጉዳይ ፈጣሪ ያላየው መስሏቸው ለፈጣሪ በጭፈራ ሙስና ወንጀል መሳተፋቸውን ለመክሰስ ነው…..? ስለዚህ የማከብራችሁና የምወዳችሁ ጦማረኞች ብትችሉ አቶ ኃይለማርያምን በጭፈራ ላይ ያላቸውን አቋም ሁኔታ ተመቻችቶላችሁ ካገኛችኋቸው ጠይቋቸውና አውነቱን እንስማ ነገር ግን በፎቶ ሾፕ በተነካካ ፎቶ ላይ ያልሆነ መረጃ ባታቀብሉን ደስ ይለኛል… አድርገውትም ከሆነ ወይ ልክ ነኝ ይሉናል ወይም ተሳስቼ ወይም አሳስተውኝ ወይም ስለዚህ ጉዳይ አብረውን ሊጠይቁን ይችላሉ… ለማንኛውም ቢጨፍሩ መብታቸው .. ካልጨፈሩም ደግሞ ጨፈሩ ብሎ ማውራቱም መብታቸው ነው… ቢጨፍሩ ለራሳቸው ወይም ለሰው እይታ ነው ከዚህ ያለፈ ምንም ፋይዳ የለውም… እንጂ ከፖለቲካ ጋር ምንም የሚገናኝ አይመስለኝም.. ምክንያቱም የትም ቦታ የትኛውም ፕሮግራም ላይ ጭር እንዳይል ሙዚቃ ይከፈታል/በተለመዱ ፕሮግራሞች ለምሳሌ የመንግስትም ሆነ የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ወይም የተለያዩ የሽልማት፣ የውድድር ፕሮግራም……ላይ ሙዚቃ አለ መንፈሳዊ ፕሮግራም እንኳ ቢሆን በመንፈሳዊኛ ይጨፈራል ሰው እንቅስቃሴ ያደርጋል/ አንዳንዱ በልቡ ይጨፍራል አንዳንዱ ተቀምጦ ይጨፍራል አንዳንዱ ደግሞ ፈልጎ ተነስቶ ይጨፍራል አንዳንዱ ደግሞ ሌላው ሲነሳ ይሉኝታ ይዞት ያጨፋፍራል ይሄ የተለመደ ነው… ስለዚህ ሰውዬው ጨፈሩም አልጨፈሩም የራሳቸው ጉዳይ ነው ለእኔም ለሃገርም ለፈጣሪም ምንም የሚጠቅም ነገር የለም … ጉዳትም የለውም እኔንም አይጎዱኝም ፈጣሪንም አይጎዱትም የኢትዮጵያ ህዝብንም የሚጎዱት አይመስለኝም በጭፈራቸው.. ይልቅ ጭፈራ አካባቢ ብዙም ባያዘወትሩና አርፈው ስራቸውን ቢሰሩና ሃገራችንን ከኋላቀርነት እንዲላቀቅ የበኩላቸውን የዜግነት ግዴታ ቢወጡ ጥሩ ነው እላለሁ፡፡ እስከዳር ዘለቀ addiszena.net
Posted on: Mon, 24 Mar 2014 05:30:45 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015