ኣፍሪካውያን ጋዜጠኞች “ሻካሮቭ - TopicsExpress



          

ኣፍሪካውያን ጋዜጠኞች “ሻካሮቭ የነጻነት ሽልማት” ተሸላሚ ለመሆን የኣገሪቱ ሕገ-መንግስት ኣደጋ ላይ መጣል ወይም ከኣሸባሪዎች ጋር በመሆን መስራት ኣንዱና ተቀዳሚ መስፈርት እስኪመስል ድረስ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙና እስክንድር ነጋ ለመጨረሻ ዕጩነት ቀርበዋል፡፡ ኣውሮፓውያኑ ኣሁንም ከኢትዮጵያውያን ራስ ኣንወርድም ብሏል፡፡ በነሱ ቅኚ ባለመገዛታችን ኣንጀታቸው እያቃጠላቸው ኣሁን ደግሞ እነሱ በሚያደርሱት ጫና ለኣንድ ሰከንድም ቢሆን ከልማቱ የማይስተጓጎል ጠንካራ ህዝባዊ መሰረት ያለው መንግስት መኖሩ የራስ ምታት እንደሆነባቸው ያሳያል፡፡ ይሄኔ ኣንዷ ኣውሮፓዊት ሃገር ኢትዮጵያን ቅኚ ገዝታ ቢሆን ኑሮ ሽንጧን ገትራ ትከራከርልን እንደነበር፡ እነሱም ይህ እንደ ኣንድ ቅኚ ኣለመገዛታችን (disadvantage) መሆኑን ማሳያ ኣድርገው እየተጠቀሙበት ነው፡፡ ሃገራችን በራሳችን ጥረት እንገነባለን፡፡ ለኣውሮፓውያን ዕርዳታና ብርድር እጃችን ኣንሰጥም፡፡ ይህ የራስ ምታት ከሆነባቸው ነገና ከነገ ወድያ ምን እንደሚሆኑ ለማየት ያብቃን፡፡
Posted on: Wed, 18 Sep 2013 07:21:17 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015