እንኳን 2006 የመጨረሻ ሰኞ በሰላም - TopicsExpress



          

እንኳን 2006 የመጨረሻ ሰኞ በሰላም አደረሳችሁ! እስከዛሬ በነበረን የ‹ከሰላምታ ጋር› ቲያትር ትርዒታችን የታደማችሁ፣ደግማችሁ ደጋግማችሁ ያያችሁንንም ሁሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለያዩ የመገናና ብዙሀን እንዲሁም ማህበራዊ ድረገፆች ስራችንን በማስተዋወቅ፣አድናቆታችሁን በመግለፅ እና በመዘገብ የተባበራችሁንን ግለሰቦች እና ተቋማት እንዲሁ እናመሰግናለን፡፡ ለስራው መሳካት፣ገንዘባችሁን ጉልበታችሁን፣ ጊዜአችሁን እና ፍቅራችሁን ለሰጣችሁ ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ 2006ዓ.ም ሳያልቅቲያትሩን ለማየት ለምትፈልጉ ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ወደ ጃዝ አምባ(ጣይቱ ሆቴል) ጎራ ቢሉ አመቱን የማይረሳ አድርገው ያሳልፉታል፡፡ የዛሬው የጳጉሜ 3 ትርቺታችን ልክ ከምሽቱ 1 ሰዓት ሲል ይጀመራል፡፡ ከ 12 ሰዓት ጀምሮ በራችን ለተመልካች ክፍት ነው፡፡ የመግቢያ ትኬዎን ከ 10 ሰዓት ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡ መጪው ዓመት በህይወት በስራችሁ ሁሉ የምትመኙትን ለውጥ የምታገኙበት የደስታ ዓመት አንዲሆንላችሁ እየተመኘን ቲያትራንን ላያችሁም ላላያችሁም ይህንን የፎቶ ቪዲዮ ጋብዘናችኋል፡፡ መልካም አዲስ አመት!
Posted on: Mon, 08 Sep 2014 10:14:52 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015