ኮሚቴዎቻችንና ወንድሞቻችን 1 የድምፅ 2 - TopicsExpress



          

ኮሚቴዎቻችንና ወንድሞቻችን 1 የድምፅ 2 የቪዲዮ በጥቅላላው ሶስት ማስረጃዎችን አቀረቡ። Via-★የቂሊንጦ ልሳን★ https://­facebook/yeqilintolisan ሃሙስ ጥር 7/2007 የሰላም አምባሳደሮቻችን የሆኑት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን እንዲሁም በአንደኛ ተከሳሽ በአቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተካተቱ ወንድሞቻችንና ዱዓቶቻችን ሴሚት በሚገኘው ቦሌ ምድብ ችሎት ቀርበው 1 የድምፅ 2 የቪዲዮ ማሰረጃቸውን አሳዩ። የቀረበው አንድ የኦዲዮ ማለትም የፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ፀጋዬ ሀ/ማርያም በኢትዮ ቻይና ካምፓስ ከስልጠና በሁዋላ ያደረጉት ንግግር እና ሁለት የቪዲዮ ማስረጃ 1 የድምፅ 2 የቪዲዮ በጥቅላላው ሶስት ማስረጃዎችን እንደቀረቡ የቂሊንጦ ልሳን ምንጮች ዘገቡ። በዛሬው ችሎት ላይ የቀረበው አንድ የድምፅ(audio) ማለትም የፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ፀጋዬ ሃ/ማርያም ያደረጉት ንግግር እንዲሁም ሁለት የቪዲዮ ማስረጃዎች ታይተዋል። የመጀመሪያው የድምፅ ማስረጃ የፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ፀጋዬ ሃ/ማርያም በኢትዮ ቻይና ካምፓስ ከስልጠና በኻላ ያደረጉት ንግግር በድምፅ የተደመጠ ሲሆን ወሃቢያን ማስወገድ አለብን፣ ወሀቢዮች እውቀት የላቸውም የሚንቀሳቀሱት ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ስላላቸው ነው፤ ፀረ-ህገመንግስት ናቸው...ወዘተ የሚሉ በሃይማኖት ምን ያህል የመንግስት አካላት ጣልቃ ገብተው እንደነበር የሚያሳይ የድምፅ መስረጃ ቀርቧል። በቀጣይም በሁለተኛው ሲዲ የቪዲዮ ማስረጃ የቀረበ ሲሆን የአወሊያ ተማሪ ሙባረክ አደም ebs ከቢላል ሾው ጋዜጠኛ ጋር ያደረገውን ውይይት አሳይቷል። በቪዲዬውም ላይ በወርሃ ጥር 2004 ኮሚቴው ከመቋቋሙ በፊት ምን እንደሚመስል የነበረውን ሁኔታገለፃ ሲያደርግ፤ የሶስቱን ጥያቄዎች አነሳስ፣ የኮሚቴውን አመራረጥ በሰፊው በትንታኔ መልክ ሲየስረዳ ታይቷል። በሶስተኛው ሲዲ ላይ በነአቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ ከተካተቱት ከህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ ኮሚቴዎችና ወንድሞቻችን መሃከል ጥር 11/2004 3,4,5,7,8 እና 9 ተከሳሾች ያደረጉትን ሰላማዊና ሃገር ወዳድ መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ በገሃድ የሚያሳይ ማስረጃ በቪዲዬው ላይ ታይቷል። በድሩ ሁሴን ሀገራችንን እንዴት መውደድ እንዳለብን ሲናገር፣ ኢስታዝ ካሚል ሸምሱ ጥያቄዎቹ ህገ መንግስታዊ መሆናቸውን ሲተነትን፣ ኢስታዝ ሙሃመድ አባተ የኹጥባ ትርጉም ሊየቀርብ ሲል ህዝቡ ሲየስቆመው፣ ኢስታዝ ያሲን ኑሩ አሀባሽ ይወገዳል አባይ ይገደባል ሲል..ወዘተ በማስረጃው ላይ ቀርቧል። የፍርድ ሂደቱም ካላለቀው ሶስተኛ ሲዲ በመጀመር ነገ ይቀጥላል። ብቸኛ አሚሮቻችን ኮሚቴዎቻችን! ፍትህ ለኮሚቴዎቻችን! የጊዜ፣ የገንዘብ፣ የዕውቀት...መስዋዕትነት ተከፍሎባቸው የሚሰሩ ዘገባዎችን ሼር እና ኮፒ በማድረግ እንዲሁም በየሰሌዳችን፣ በየጉረፑ፣ በየፔጁ በመለጠፍ መረጃውን ለሰፊው ማህበረሰባችን በማሰራጨት ኢስላማዊ ግዴታዎን ይወጡ!!!! ይጠቀማሉ!!! ኢንሻ አላህ። ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩ ተጨማሪ መረጃዎችን እና ወቅታዊ ዜናዎችን ለማግኝት ይህንን ገፅ ላይክ ያድርጉ የቂሊንጦ ልሳን- የኢትዮጲያዊያን ሙስሊሞች ድምፅ https://­facebook/yeqilintolisan
Posted on: Thu, 15 Jan 2015 11:24:58 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015