የጆካ ባሪቅ(የጆካ አባቶች) የጆካ ማለት - TopicsExpress



          

የጆካ ባሪቅ(የጆካ አባቶች) የጆካ ማለት የቦታ ስም ሲሆን ባሪቅ ቀጥተኛ የአማርኛ ትረጉሙ ሽማግሌ ማለት ነው፡፡ ከላይ በቅንፍ ውስጥ አባቶች ያልኩበት ምክንት፡ ሽማግሌ ብል ቀጥታ ስለማርጀት ያወራሁኝ እንዳይመስልብኝ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ አባቶች( ከሰባት ቤት ጉራጌ የሚወጣጡ ናቸው)፡ ዋነኛ ስራቸው ባህላዊ ማለቴ የጉራጌ ባህልን ጠብቀው የሚያኖሩ ናቸው፡፡ አዋጆችን ያወጣሉ እንዲሁም ቀጥተኛና ተፈጻሚ የሚሆን የዳኝነት ፍርድ ይፈርዳሉ፡፡ ማንም ሰው እነዚህ አባቶች ያወጡት አዋጅ አይሽርም፡፡ እና ይህን ተሰብስበው የሚወስኑት ማንኛውንም ምክክርና አዋጅ ቒጫ ተብሎ ይጠራል ቦታው ደግሞ የጆካ ይባላል፡፡ ወደፊት ስለ የጆካ ባሪቅ ብዙ እንባባላለን፡፡
Posted on: Mon, 04 Nov 2013 17:19:15 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015