ጉዳዩ ፡-ለኡስታዝ ሀሰን ታጁ የእፎይታ - TopicsExpress



          

ጉዳዩ ፡-ለኡስታዝ ሀሰን ታጁ የእፎይታ ጊዜ እንዲሰጣቸው ምክረ ሃሳብ ስለማቅረብ ከሙስሊም ወዳጄ(Muslim Wedaje) ለመንግስት ብቻ ሳይሆን ለኡስታዝ ሐሰን ታጁም የእፎይታ ጊዜ ሊሰጣቸው ይገባል!! ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች በርካታ ኢስላማዊ መጽሃፍቶችን በአማርኛ በማቅረብ ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው እና መርዛማ የሆነውን የውጪ ሃገር ትምህርት ቀስመው ያልመጡት ኡስታዝ ሐሰን ታጁ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የነካቸው ነገር በመውል ባይታወቅም መንገድ ስተው በመውጣታቸው ፍሬኑን መቆጣጠር ተስኗቸው ከህዝብ ጋር መላተማቸው የሚታወስ ነው፡፡ይህንንም ተከትሎ ደግሞ በአደባባይ ህትመት ቤት ስለሌላቸው መፅሃፍ ማሳተም እና መቸብቸብ ያልቻሉ ፀኃፊ ወንድሞች የኡስታዝ ሀሰን ታጁን ክፉኛ ከመስመር መውጣት አሳስቧቸው በተረባረበ ክንድ ጠላት ጥቃት የፈፀመ እስኪመስል ድረስ በከባባድ ብዕር ኡስታዝዬን ሸከሸኳቸው፡፡ በእርግጥ እነዚህ ብዕረኞች ኡስታዝዬን ላቀረቡት እና ለሰነዘሩት አብዬታዊ የሃሳብ ጥቃት ተመጣጣይ የሆነ አፀፋ ሳይሆን የሃይል ሚዛኑን ባልጠበቀ መልኩ ኡስታዝዬን አብዬታዊ ጋሻ አላቸው በሚል ነው መሰለኝ ሽከሽክ ያደረጉበትን ፅሁፎች ማተሚያ ቤት ስለሌላቸው አሳትመው ለህዝብ እንዲደርስ በነፃ አላከፋፈሉም፡፡የሆኖ ሆኖ ግን በሰሞኑ ኡስታዝዬ ፋክት ለተባለችው መጽሔት በሰጡት ቃለ መጠይቅ የአብዬታዊው ግንባር ዘብ ሆነው ኡማውን አንዴ ወዲህ አንዴ ወድያ እያሉ በመንታ መንገድ ላይናችሁ ለሚለው ምክረ ሃሳባቸው የደረሰባቸውን ክሽከሻ ለመበቀል በሚመስል መልኩ የምላስ ወለምታቸውን ከውስጥ ያለው ኢጎን መቆጣጠር እቅቷቸው ጋዜጠኛው ሳይቀር እንሲገረምባቸው ድረስ ሲወርፉን እና ኡማውን በአብዬታዊ ቅላፄ ሲያንሸዋርሩት ተመለከተናል፡፡ውሎ ሳያድር እነዛ የሃይል ሚዛን ባልጠበቀ መልኩ ጥቃት የሚፈፅሙት ልጆች ሁሌም በሚያጠቁበት ብዕራቸው ኡስታዝዬ ካፈርኩ አይመልኝ በሚል ብሂላቸው ለፋክት መፅሄት ለሰጡት ቃለ መጠይቅ ምንም የማያንፈራግጥ ምለሽ ሰጧቸው፡፡እኔስ ከሁሉ ያስገረመኝ ብሎም ለኡስታዝዬ በፍፁም አይገባቸውም ያልኩት ረያን ዘ ሃበሻ የተባለ ታዳጊ ፀሃፊ አላርፍ ላሉት እስታዜ ከድሮ ጀምሮ በውስጡ ያስቀመጣትን ፈንጂ እላያቸው ላይ ለቀቀባቸው፡፡ ከምር የሚተርፉም አልመሰለኝም፡፡ ለዛም ነው እኮ እረ በቃ ለሳቸውም የእፎታ ጊዜ ይሰጣቸው ስል ተማፅኖዬን ለናንተ ያቀረብኩት፡፡ በኡስታዝዬ ላይ ለደረሰው ያልተመጣጠነ የሃይል ጥቃት ከዚህ ቀደም ለዋሉት ውለታ(በአሁኑ ወቅት የሰሩትን መልካም ስራ ለአብዬታዊ የልማት አጀንዳ ሊመነዝሩት መሞከራቸው የሚታወስ ነው) ታሳቢ በማድረግ ልለተወሰነ ጊዜ የእፎይታ ጊዜ እንዲሰጣቸው እና በስነ ልቦና ተጎድተው ወደነበሩበት የመፅሃፍ ህትመት አስተዋፅኦቸው ከመመለስ እንደያግዳቸው ስል ይህን ምክረ ሃሳብ ተቀበሉኝ ስል እማፀናችኋለው፡፡ ከምር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ አሳዘኑኝ፡፡ ባጋጣሚ ዩ ቲዩብ ስጎረጉር የሳቸውን ትምህርት አገኘውና በደንብ አድርጌ ኮመኮምኩት፡፡ ወላሂ በጣም እኮ አንደበተ ርቱ እና አስገራሚ ዳኢ ነበሩ፡፡በአካልም ተገኝቼ ዳዕዋ ሲያደርጉ ተከታትዬ አውቃለው፡፡ አፍ ያስከፍተ ነበር ሲያስተምሩ፡፡ ወላሂ ምን አይነት አብዬታዊ ቡዳ እንደበላቸው አላውቅም፡፡ ይህን የመሰለ ታላቅ እና አንደበተ ርቱ ሰው አንዴት ለአብዬታዊ ቡዳ ይንበረከካል???? ምንኛ ከባድ ቢሆን ነው ባካችሁ አብዬታዊ ጂኒ እንዲህ ቁልፍልፍ አድርጎ አንደበተ ርቱነታቸው እና ከባዱ ብዕራቸውን ሽባ ያደረገው??? በመፅሃፎቻቸው እንደጉድ ፃፉት፣በዳዕዋቸው እንደጉድ ተናገሩን መከሩን ገሰፁን፣ በብዕራቸው ለፍጡራን እንዳናጎበድድ፣ ሙስሊም ጠንካራ፣ለአቋሙ የፀና ስለመሆኑ ሰበኩን፣የነብዩን(ሰ፣ዐ፣ወ) ሲራ እወቁ ሲሉ ፃፉልን ተረጎሙልን፣ስለ ቀደምት ሰለፎች ፅናት እና ብርታት፣የትግል ጀግኖች ዘከሩልን፣በቅዱስ ቁርአን ትርጉም ማባራሪያው ደግሞ ስለትግል አስፈላጊነት ብሎም በፅናት እስከ ዕለተሞት መታገል እንደሚገባን አስገነዘቡን፡፡ ታዲያ ምን ያደርጋል መናገሩን እና መፃፉን እንደጉን ቻሉበት፡፡ ተግባሩ ላይ ግን ኡሰታዝዬ ተሸበለሉብን፡፡ እረ ወዳጆቼ ዱአ እናድረግላቸው በፍፁም አብዬታዊ ጎርፍ አይናችን እያየ ሲወስዳቸው ዝም ማለት የለብንም፡፡ ደሞ እኮ ኡስታዝ ሐሰን ታጁ አብዬታዊው ልክፍት ሳይለክፋቸው በፊት ሃይባቸው ያስፈራ ነበር፡፡ በሆነ አጋጣሚ እሳቸው በተጠሩበት ቦታ እኔም በቦታው ከተገኘው አጠገባቸው ቁጭ ካልኩኝ አጠገቤ ካለው ሰው ጋር እንኳን አላወራም ነበር፡፡ ቀና ብዬ ራሳቸውን ሳያቸው ገና የተረጎሙት መፅሃፍ፣በእጃቸው የፃፉት መፅሃፍቶች እንዲሁም ያነበቡትን መፅሃፎቶች እያስተነተንኩኝ ምን ያህል አላህ ቢረዳቸው ይሆን እንዲ አስገራሚ የሆኑት ብዬ እገረም ነበር፡፡ ምን ያደርጋል ታዲያ አብዬታዊው ጎርፍ እሳቸውንም በሽውታ መልኩ ዞር እድርጎባቸው ሄደና ይኸው ኡማውን አንዴ መንታ መንገድ ,አንዴ ማሳለጫ መንገድ ,አንዴ ቀለበት መንገድ አንዴ በፋክት መፅሄት ብቅ እያሉ ጃስ እያሉ ይለክፉታል፡፡ ከምር አብዬታዊው ልክፍት ጨካኝ ነው፡፡ ከሚወደቻው ፣ከሚያከብራቸው ኡማ ነጠላቸው፡፡ የተከበሩትን እና የተወደሱትን ያህል በአብዬታዊው ቡዳ ግፊት በህዝበ እንዲተፉ አደረጋቸው፡፡ ቲሽ ወላሂ ተናደድኩኝ፡፡ በፍፁም ኡስታዝ ሀሰን ታጁ ሊበገሩ የሚገባቸው ሰው አልነበሩም፡፤ አሁንም አላህ ይመልሳቸው ስል ዱአዬን እቀጥላለው፡፤ ከምር ከልቤ አሳዝነውኛል፡፡ ኡስታዝዬ አኡዙቢላህ ብለው ከአብዬታዊው ልክፍት እራሶን ያላቁ ዘንድ እጠይቆታለው፡፡ የኛዎቹ ደግሞ የሃይል ሚዛኑን ባልጠበቀ መልኩ እየሰነዘራችሁ ያላችሁትን ጥቃት ኡስታዝዬን እጅጉኑ ደማቸውን እያፈላ ወደ ወጣትነት እየገፋፋቸው ስለሆነ ትንሽ ቆም ብለው ያስቡበት ዘንዳ ለመንግስትዬ የሰጠነውን አይነት የማሰቢያ ጊዜ ለኡስታዝዬም ጀባ እንበላቸው፡፤ እፎይታ ጊዜ ለመንግስት ብቻ ነው የሚሰጠው ያለው ማነው???? በመጨረሻም ደግሞ ይህን እፎያታ ጊዜ ይሰጣቸው ብዬ ወዳጆቼን የተማፀንኩት ኡስታዝ ሃሰንዬ ስለሆኑ እንጂ ሌላው ቢሆንማ ጊዜም የለን ለወሬያቸው……….. አላህ ቸር ያሰማን
Posted on: Thu, 03 Oct 2013 04:13:49 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015